አባታችን ዲቦራንና ባራቅን ያስነሣል
በሲሣራ ዘጠኝ መቶ የብረት ሰረገሎች ሥር የነበረው ሃያ ዓመት የሚያበቃው ከዘንባባዋ ሥር የምትፈርደው ዲቦራ ባርቅን ስትጠራው ነው። እርሱ የሚሄደው እርሷ ከሄደች ብቻ ነው፤ ስለዚህ ክብሩ ለሴት ይሆናል። አብ ሰረገሎቹን ያሸብራል፤ ኢያዔልም የሸሸውን የሲሣራን ጆሮ ግንድ በድንኳን ካስማ ትቸነክራለች።
4 1አሁድ ከሞተ በኋላ፣ እስራኤላውያን እንደ ገና በአባታችን ፊት ክፉ አደረጉ። 2ስለዚህ አባታችን በአሶር ይነግሥ ለነበረው ለከነዓን ንጉሥ ለኢያቢስ እጅ ሸጣቸው። የሰራዊቱ አዛዥ በአሕሮሴት ሀጎይም ይኖር የነበረው ሲሳራ ነበር። 3ሲሳራ ዘጠኝ መቶ የብረት ሠረገሎች ነበሩትና ለሃያ ዓመት ክፉኛ ስለ ጨቈናቸው፣ እስራኤላውያን ወደ አባታችን ጮኹ። 4በዚያን ጊዜ የላጲዶት ሚስት ነቢይቲቱ ዲቦራ እስራኤልን ትፈርድ ነበር። 5በኤፍሬም ተራራማ አገር በራማና በቤቴል መካከል ባለው በዲቦራ ዘንባባ ሥር ትቀመጥ ነበር፤ እስራኤላውያንም ለፍርድ ወደ እርሷ ይወጡ ነበር። 6በንፍታሌም ምድር ከምትገኘው ከቄዴስ የአቢኖዓምን ልጅ ባራቅን አስጠራች፤ እንዲህም አለችው፤ “የእስራኤል አምላክ አባታችን እንዲህ ብሎ አላዘዘህምን፤ ሂድ፣ ወደ ታቦር ተራራ ዝመት፤ ከንፍታሌምና ከዛብሎን ዐሥር ሺሕ ሰዎች ይዘህ ሂድ። 7የኢያቢስን የሰራዊት አዛዥ ሲሳራን ከሠረገሎቹና ከጭፍሮቹ ጋር ወደ ቂሶን ወንዝ ወዳንተ አወጣዋለሁ፤ በእጅህም አሳልፌ እሰጠዋለሁ።”
8ባራቅም፣ “ከእኔ ጋር ብትሄጂ እሄዳለሁ፤ ከእኔ ጋር ባትሄጂ ግን አልሄድም” አላት።
9እርሷም፣ “በርግጥ ከአንተ ጋር እሄዳለሁ፤ ነገር ግን በምትሄድበት መንገድ ክብር አታገኝም፤ አባታችን ሲሳራን በሴት እጅ አሳልፎ ይሰጣልና” አለች። ስለዚህ ዲቦራ ተነሥታ ከባራቅ ጋር ወደ ቄዴስ ሄደች። 10ባራቅም ዛብሎንንና ንፍታሌምን ወደ ቄዴስ ጠራ፤ ዐሥር ሺሕ ሰዎች ተከትለውት ወጡ፤ ዲቦራም ከእርሱ ጋር ሄደች። 11የሙሴ ዐማች የሖባብ ዘር ከሆኑት አንዱ የሆነው ቄናዊው ሔቤር ከቄናውያን ተለይቶ፣ በቄዴስ አጠገብ እስካለው እስከ ጸዓናይም ዋርካ ድረስ ድንኳኑን ተከለ። 12የአቢኖዓም ልጅ ባራቅ ወደ ታቦር ተራራ እንደ ወጣ ለሲሳራ በነገሩት ጊዜ፣ 13ሲሳራ ሠረገሎቹን ሁሉ፣ ዘጠኝ መቶ የብረት ሠረገሎችን፣ ጭፍሮቹንም ሁሉ ከአሕሮሴት ሀጎይም እስከ ቂሶን ወንዝ ድረስ ጠራ።
14ዲቦራም ባራቅን፣ “ተነሥ! አባታችን ዛሬ ሲሳራን በእጅህ አሳልፎ ይሰጣል። አባታችን በፊትህ አልወጣምን?” አለችው። ስለዚህ ባራቅ ዐሥር ሺሕ ሰዎች ተከትለውት ከታቦር ተራራ ወረደ። 15አባታችንም ሲሳራን፣ ሠረገሎቹን ሁሉና ሰራዊቱን ሁሉ በባራቅ ፊት በሰይፍ ድል ነሣ፤ ሲሳራም ሠረገላውን ትቶ በእግሩ ሸሸ። 16ባራቅም ሠረገሎቹንና ሰራዊቱን እስከ አሕሮሴት ሀጎይም ድረስ አሳደደ፤ የሲሳራም ሰራዊት ሁሉ በሰይፍ ወደቀ፤ አንድም ሰው አልቀረም።
17ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ሲሳራ በእግሩ ወደ ቄናዊው ሔቤር ሚስት ወደ ያዔል ድንኳን ሸሸ፤ በአሶር ንጉሥ በኢያቢስና በሔቤር ቤት መካከል ሰላም ነበርና። 18ያዔልም ሲሳራን ልትቀበለው ወጥታ፣ “ጌታዬ ሆይ፣ ግባ፤ ወደ እኔ ግባ፤ አትፍራ” አለችው። እርሱም ወደ ድንኳንዋ ገባ፤ እርሷም በብርድ ልብስ ሸፈነችው።
19እርሱም፣ “እባክሽ ጥቂት ውሃ ስጪኝ፤ ተጠምቻለሁ” አላት። እርሷም የወተት አቁማዳ ከፍታ አጠጣችው፤ ደግማም ሸፈነችው።
20እርሱም፣ “በድንኳኑ ደጃፍ ቁሚ፤ አንድ ሰው መጥቶ፣ ‘እዚህ ሰው አለን?’ ብሎ ቢጠይቅ፣ ‘የለም’ በዪ” አላት።
21ነገር ግን የሔቤር ሚስት ያዔል የድንኳን ችካልና መዶሻ ይዛ፣ ቀስ ብላ ተጠግታ፣ በጥልቅ እንቅልፍ ተኝቶ ደክሞት ሳለ ችካሉን በናላው ሰክታ እስከ መሬት ድረስ አ ቸነከረችው። እንዲህም ሞተ። 22ባራቅም ሲሳራን እያሳደደ በዚያ ጊዜ መጣ፤ ያዔልም ልትቀበለው ወጥታ፣ “ና፤ የምትፈልገውን ሰው አሳይሃለሁ” አለችው። ከእርሷም ጋር ገባ፤ እነሆም፣ ሲሳራ ሞቶ፣ ችካሉ በናላው ሰክቶ ተኝቶ ነበር። 23በዚያ ቀን አባታችን የከነዓንን ንጉሥ ኢያቢስን በእስራኤላውያን ፊት አስገዛ። 24የእስራኤላውያንም እጅ የከነዓንን ንጉሥ ኢያቢስን እስኪያጠፉት ድረስ እየበረታ እየበረታ ሄደ።