አብርሃምና ኬጡራ
አብርሃም ይሞታል፤ ተለያይተው የነበሩት ሁለቱ ልጆቹም አብረው ይቀብሩታል። አብ ይስሐቅን ይባርካል። ከዚያም የርብቃ መንታዎች ከመወለዳቸው በፊት ይታገላሉ፤ ፈጽሞም አያቆሙም፦ ዔሳው ከሜዳ ተርቦ ይመጣል፣ ብኵርናውንም በወጥ ይለውጣል፣ ምንም እንዳልሆነም ይቈጥረዋል።
25 1አብርሃም ኬጡራ የተባለች ሌላ ሚስት አገባ። 2እርሷም ዘንበራንን፣ ዮቅሳንን፣ ሞዳንን፣ ምድያምን፣ አይሷቅንና ሱሐን ወለደችለት። 3ዮቅሳን ሳባንና ድዳንን ወለደ። የድዳን ልጆች አሦራውያን፣ ለጡሳውያንና ለኡማውያን ነበሩ። 4የምድያም ልጆች ኤፋ፣ ኤፌር፣ ሄኖክ፣ አቢዳዕና ኤልዳዓ ነበሩ፤ እነዚህ ሁሉ የኬጡራ ልጆች ናቸው። 5አብርሃም ያለውን ሁሉ ለይስሐቅ ሰጠ። 6አብርሃም ገና በሕይወት ሳለ ለቁባቶቹ ልጆች ስጦታ ሰጠ፤ ከዚያም ከልጁ ከይስሐቅ ዘንድ አርቆ ወደ ምሥራቅ አገር፣ ወደ ፀሓይ መውጫ ላካቸው።
7አብርሃም በጠቅላላው 175 ዓመት ኖረ። 8አብርሃም በመልካም ሽምግልና፣ ዕድሜው ጠግቦ ሽማግሌ ሆኖ ነፍሱን ሰጠ፤ ወደ ወገኖቹም ተሰበሰበ። 9ልጆቹ ይስሐቅና እስማኤል በመምሬ አጠገብ ባለው፣ በኬጢያዊው በሱሐር ልጅ በ ኤፍሮን እርሻ ውስጥ ባለችው በመክፈላ ዋሻ ቀበሩት። 10ይህች እርሻ አብርሃም ከኬጢያውያን የገዛት ናት። አብርሃም ከሚስቱ ከሣራ ጋራ በዚያ ተቀበረ። 11አብርሃም ከሞተ በኋላ አባታችን ልጁን ይስሐቅን ባረከ። ይስሐቅም በብኤርለሃይሮኢ አጠገብ ተቀመጠ።
የእስማኤል ትውልድ
12የግብፃዊቷ የሣራ አገልጋይ የሆነችው አጋር ለአብርሃም የወለደችለት፣ የአብርሃም ልጅ የእስማኤል የትውልድ ታሪክ ይህ ነው። 13የእስማኤል ልጆች ስም በተወለዱበት ቅደም ተከተል ይህ ነው፤ የእስማኤል የበኵር ልጅ ነባዮት፣ ቀጥሎም ቄዳር፣ አድብኤል፣ ሚብሳም፣ 14ሚሽማ፣ ዱማ፣ ማሳ፣ 15ሐዳድ፣ ቴማ፣ ይጡር፣ ናፊስና ቄድማ ናቸው። 16እነዚህ የእስማኤል ልጆች ናቸው፤ እነዚህም በየመንደራቸውና በየሰፈራቸው ስማቸው ነው፤ እንደ ነገዳቸውም ዐሥራ ሁለት አለቆች ነበሩ። 17እስማኤል 137 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ነፍሱን ሰጠ፤ ሞተም፤ ወደ ወገኖቹም ተሰበሰበ። 18ከኤውላጥ አንሥቶ እስከ ሱር ድረስ፣ ከግብፅ ምሥራቅ ወደ አሦር አቅጣጫ ተቀመጡ፤ እስማኤልም ከዘመዶቹ ሁሉ ጋራ በጥል ኖረ።
የይስሐቅ ዘር
19የአብርሃም ልጅ የይስሐቅ የትውልድ ሐረግ ይህ ነው፤ አብርሃም ይስሐቅን ወለደ። 20ይስሐቅ የሶርያዊውን የ ላባን እኅት፣ የ ጳዳን አራም ሶርያዊ የቤቱኤል ልጅ የሆነችውን ርብቃን ባገባ ጊዜ ዕድሜው አርባ ዓመት ነበር። a a v20 ጳዳን አራም በሁለቱ ወንዞች መካከል ባለው ምድር የሚገኝ የሶርያ ኰረብታማ ሜዳ፣ የርብቃ ቤተ ዘመድ የትውልድ አገር ነበር። 21ይስሐቅ ሚስቱ መካን ስለ ነበረች ስለ እርሷ አባታችንን ለመነ፤ አባታችንም ጸሎቱን ሰማ፤ ሚስቱም ርብቃ ፀነሰች። 22ነገር ግን ልጆቹ በማኅፀኗ ውስጥ እርስ በርስ ይገፋፉ ነበር፤ እርሷም፣ “እንዲህ ከሆነ፣ ይህ ለምን ይደርስብኛል?” አለች። ስለዚህ አባታችንን ልትጠይቅ ሄደች።
23አባታችንም እንዲህ አላት፤ “ሁለት ሕዝቦች በማኅፀንሽ ውስጥ አሉ፤ ሁለት ወገኖችም ከውስጥሽ ተለያይተው ይወጣሉ፤ አንዱ ከሌላው ይበረታል፤ ታላቁም ለታናሹ ይገዛል።”
24የመውለጃዋ ጊዜ በደረሰ ጊዜ፣ እነሆ በማኅፀኗ ውስጥ መንታ ልጆች ነበሩ! 25መጀመሪያ የወጣው ቀይ ነበር፤ መላ ሰውነቱም እንደ ጠጕር ልብስ ነበር፤ ስለዚህ ዔሳው ብለው ጠሩት። 26ቀጥሎም ወንድሙ እጁ የዔሳውን ተረከዝ ይዞ ወጣ፤ ስለዚህ ያዕቆብ ተባለ። እነርሱን በወለደች ጊዜ ይስሐቅ ዕድሜው ስድሳ ዓመት ነበር። b b v26 ያዕቆብ የሚለው ስም “ተረከዝ ይይዛል” ማለት ነው፤ ታሪኩም እንደሚያሳየው ይህም “ይተካል” ወይም “ያታልላል” ማለት ነው።
27ልጆቹም አደጉ። ዔሳው የተካነ አዳኝ፣ የሜዳ ሰው ሆነ፤ ያዕቆብ ግን ጭምት ሆኖ በድንኳን ይኖር ነበር።
ያዕቆብና ዔሳው
28ይስሐቅ የዱር አውሬ ሥጋ ያስደስተው ስለ ነበር ዔሳውን ይወድ ነበር፤ ርብቃ ግን ያዕቆብን ትወድ ነበር። 29ዔሳው ከሜዳ በመጣ ጊዜ ያዕቆብ ወጥ ይሠራ ነበር፤ እርሱም በራብ ዝሎ ነበር። 30ዔሳውም ያዕቆብን፣ “በራብ ዝያለሁና ይህን ቀዩን ወጥ ጎርሼ ልዋጥ!” አለው። ስለዚህ ኤዶም ተባለ። c c v30 ኤዶም “ቀይ” ማለት ነው፤ ዔሳው የብኵርናውን መብት በለወጠበት በቀዩ ወጥ ምክንያት እንዲህ ተባለ።
31ያዕቆብም፣ “አሁኑኑ የብኵርናህን መብት ሽጥልኝ” አለው። d d v31 የብኵርና መብት ለበኵር ልጅ ዕጥፍ የውርስ ድርሻንና የቤተ ሰቡን አለቅነት ይሰጠው ነበር።
32ዔሳውም፣ “እነሆ፣ ልሞት ነው፤ የብኵርና መብት ምን ይጠቅመኛል?” አለ።
33ያዕቆብም፣ “አስቀድመህ ማልልኝ” አለው። እርሱም ማለለት፤ የብኵርናውንም መብት ለያዕቆብ ሸጠ።
34ያዕቆብም ለዔሳው እንጀራና የምስር ወጥ ሰጠው፤ እርሱም በላ፤ ጠጣ፤ ተነሥቶም ሄደ፤ ዔሳውም የብኵርናውን መብት ናቀ።