ጦርነት ከፍልስጥኤማውያን ጋር ተነሣ
ዮናታን አንድ የጦር ሰፈር መታ፤ ፍልስጥኤማውያን ቍጥር የሌላቸውን ሠረገሎች ይዘው ተሰበሰቡ፤ እስራኤልም ሰይፍ የሚሠራ አንጥረኛ እንኳ ሳይኖረው በዋሻዎች ተደበቀ። ሳኦል ሠራዊቱ ሲበተን እያየ ከመጠበቅ ይልቅ መሥዋዕቱን ራሱ አቀረበ። የአብን ትእዛዝ አልጠበቀም፤ መንግሥቱ አይጸናም።
13 1ሳኦል በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበር፤ በእስራኤልም ላይ አርባ ሁለት ዓመት ነገሠ። a a v1 በዚህ ቍጥር ውስጥ ያሉት ቍጥሮች ከዕብራይስጡ ጠፍተዋል፤ ዕብራይስጡ “ሳኦል የአንድ ዓመት ልጅ ነበር … ሁለት ዓመትም ነገሠ” ይላል። እዚህ ያሉት ቍጥሮች አብዛኞቹ የዘመናችን መጻሕፍት ቅዱሳት የተከተሉትን ንባብ ይከተላሉ። 2ሳኦልም ከእስራኤል ሦስት ሺህ ሰዎች መረጠ፤ ሁለት ሺዎቹ በሚክማስና በቤቴል ተራራማ አገር ከእርሱ ጋር፣ አንድ ሺዎቹ በብንያም ግብዓ ከዮናታን ጋር ነበሩ። የቀሩትንም እያንዳንዱን ወደ ድንኳኑ ሰደዳቸው። 3ዮናታንም በጌባ የነበረውን የፍልስጥኤማውያን ጦር ሰፈር መታ፤ ፍልስጥኤማውያንም ሰሙ። ሳኦልም፣ “ዕብራውያን ይስሙ!” ብሎ በምድሪቱ ሁሉ መለከት ነፋ። 4እስራኤልም ሁሉ ሳኦል የፍልስጥኤማውያንን ጦር ሰፈር እንደ መታ፣ እስራኤልም ለፍልስጥኤማውያን አስጸያፊ እንደ ሆነ ሰማ። ሕዝቡም በጌልገላ ወደ ሳኦል ተሰበሰቡ። 5ፍልስጥኤማውያንም እስራኤልን ለመውጋት ተሰበሰቡ፤ ሦስት ሺህ ሰረገሎች፣ ስድስት ሺህ ፈረሰኞች፣ እንደ ባሕር ዳር አሸዋ የማይቈጠር ሠራዊትም ነበራቸው። ወጥተውም በቤትአዌን ምሥራቅ በሚክማስ ሰፈሩ። 6የእስራኤልም ሰዎች በጭንቅ ላይ እንዳሉ ባዩ ጊዜ፣ ሕዝቡም እጅግ ተጨንቆ ነበርና፣ በዋሻዎች፣ በቍጥቋጦዎች፣ በዐለቶች፣ በጕድጓዶችና በውሃ ጕድጓዶች ተሸሸጉ። b b v6 የውሃ ጕድጓዶች የዝናብ ውሃ ለመሰብሰብና ለማከማቸት ከዐለት የተፈለፈሉ ከመሬት በታች ያሉ ገንዳዎች ነበሩ። 7አንዳንድ ዕብራውያንም እንኳ ዮርዳኖስን ተሻግረው ወደ ጋድና ወደ ገለዓድ ገቡ። ሳኦል ግን በጌልገላ ቀረ፤ ሕዝቡም ሁሉ እየተንቀጠቀጡ ተከተሉት።
ሳኦል ያለ አብ ቃል አደረገ
8ሳሙኤል በወሰነው ጊዜ መሠረት ሰባት ቀን ጠበቀ፤ ሳሙኤል ግን ወደ ጌልገላ አልመጣም፤ ሕዝቡም ከእርሱ ተበተኑ። 9ሳኦልም፣ “የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የደኅንነት መሥዋዕቶችን አምጡልኝ” አለ። የሚቃጠለውንም መሥዋዕት አቀረበ።
10የሚቃጠለውንም መሥዋዕት ማቅረብ እንደ ጨረሰ፣ ሳሙኤል መጣ፤ ሳኦልም ሊቀበለውና ሰላም ሊለው ወጣ። 11ሳሙኤልም፣ “ምን አደረግህ?” አለ። ሳኦልም መልሶ እንዲህ አለ፤ “ሕዝቡ ከእኔ ሲበተን አየሁ፤ አንተም በተወሰነው ጊዜ አልመጣህም፤ ፍልስጥኤማውያንም በሚክማስ ይሰበሰቡ ነበር፤
12‘ፍልስጥኤማውያን በጌልገላ ይመጡብኛል፤ እኔም የአባታችንን ሞገስ አልለመንሁም’ ብዬ አሰብሁ፤ ስለዚህ ራሴን አስገድጄ የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቀረብሁ።”
13ሳሙኤልም ሳኦልን፣ “ሞኝነት አደረግህ” አለው። “አባትህ ያዘዘህን ትእዛዝ አልጠበቅህም፤ ጠብቀኸው ቢሆን ኖሮ፣ አባታችን መንግሥትህን በእስራኤል ላይ ለዘላለም ባጸና ነበር፤ 14ነገር ግን አሁን መንግሥትህ አይጸናም። አባታችን እንደ ልቡ የሆነ ሰው ለራሱ ፈልጓል፤ ያዘዘህንም ስላልጠበቅህ በሕዝቡ ላይ ገዥ አድርጎ ሾሞታል።”
15ሳሙኤልም ከጌልገላ ተነሥቶ በብንያም ወዳለው ወደ ግብዓ ወጣ። ሳኦልም ከእርሱ ጋር ያሉትን ሕዝብ ቈጠረ፤ ስድስት መቶ ሰዎች ያህል ነበሩ።
እስራኤል ያለ መሣሪያ ቀረ
16ሳኦል፣ ልጁ ዮናታንና ከእነርሱ ጋር ያለው ሕዝብ በብንያም ባለው በጌባ ቈዩ፤ ፍልስጥኤማውያን ግን በሚክማስ ሰፈሩ። 17ወራሪዎችም ከፍልስጥኤማውያን ሰፈር በሦስት ቡድን ወጡ። አንደኛው በሹዓል ምድር ወዳለው ወደ ዖፍራ አቀና፤ 18ሌላው ወደ ቤትሖሮን አቀና፤ ሦስተኛውም የጸቦይምን ሸለቆ ወደሚመለከተው ድንበር፣ ወደ በረሃው አቀና። 19በእስራኤልም ሁሉ አንድ አንጥረኛ እንኳ አልተገኘም፤ ፍልስጥኤማውያን፣ “ያለዚያ ዕብራውያን ሰይፍ ወይም ጦር ይሠራሉ” ብለው ነበርና። 20ስለዚህ እስራኤል ሁሉ ማረሻቸውን፣ ዶማቸውን፣ መጥረቢያቸውንና ማጭዳቸውን ለማስሳል ወደ ፍልስጥኤማውያን ይወርዱ ነበር። 21ዋጋውም ማረሻ፣ ዶማና ሹካ ለማስሳል ሩብ አውንስ ያህል ብር፣ መጥረቢያ ለማስሳልና መውጊያዎችን እንደ ገና ለማሾል ስምንተኛ አውንስ ያህል ነበር። c c v21 መውጊያ ከብቶች እንዲንቀሳቀሱ ለመጐትጎት የሚያገለግል የተሳለ የብረት ጫፍ ያለው ረጅም በትር ነበር። 22በጦርነቱም ቀን ከሳኦልና ከዮናታን ጋር ባሉት ሕዝብ ሁሉ ዘንድ ሰይፍም ሆነ ጦር አልተገኘም፤ ሳኦልና ልጁ ዮናታን ብቻ ነበሯቸው።
23የፍልስጥኤማውያንም ጭፍራ ወደ ሚክማስ መተላለፊያ ወጣ።