ወደ ቤቴል መመለስ
ወደ ቤቴል ተመልሶ እንዲመጣ የተጠራው ያዕቆብ ቤተሰቡ አሁንም የያዙትን ባዕዳን አማልክት ቀበረ። አብ እስራኤል የሚለውን ስም አጸና። ከዚያም ኪሳራ በኪሳራ ላይ ተደራረበ፤ ሞግዚቱ ሞተች፣ ራሔል ብንያምን ስትሰይም ሞተች፣ ሮቤል የአባቱን መኝታ አረከሰ፣ ይስሐቅም ተቀበረ።
35 1ከዚያም አባታችን ያዕቆብን እንዲህ አለው፤ “ተነሥተህ ወደ ቤቴል ውጣ፤ በዚያም ተቀመጥ፤ ከወንድምህ ከዔሳው በሸሸህ ጊዜ ለተገለጥሁልህ ለእኔ በዚያ መሠዊያ ሥራ።”
2ያዕቆብም ለቤተ ሰዎቹና ከእርሱ ጋር ላሉት ሁሉ እንዲህ አለ፤ “በመካከላችሁ ያሉትን የባዕድ አማልክት አስወግዱ፤ ራሳችሁን አንጹ፤ ልብሳችሁንም ለውጡ። 3ተነሥተን ወደ ቤቴል እንውጣ፤ በመከራዬ ቀን ለመለሰልኝ፣ በሄድሁበትም ሁሉ አብሮኝ ለነበረው ለአባታችን በዚያ መሠዊያ እሠራለሁ።”
4በእጃቸው የነበሩትን የባዕድ አማልክት ሁሉ፣ በጆሮአቸውም የነበሩትን ጒትቻዎች ለያዕቆብ ሰጡት፤ እርሱም በሴኬም በሚገኘው የአድባር ዛፍ ሥር ደበቃቸው። 5ከዚያም ተነሡ፤ በዙሪያቸው ባሉት ከተሞች ላይ ከአባታችን የመጣ ድንጋጤ ወደቀባቸው፤ ስለዚህ ማንም የያዕቆብን ልጆች አላሳደዳቸውም። 6ያዕቆብም ከእርሱ ጋር ከነበሩት ሰዎቹ ሁሉ ጋር በከነዓን ምድር ወዳለችው ወደ ሉዝ ማለትም ወደ ቤቴል መጣ። 7በዚያም መሠዊያ ሠራ፤ ከወንድሙ በሸሸ ጊዜ አባታችን በዚያ ራሱን ለያዕቆብ ስለገለጠለት ስፍራውን ኤልቤቴል ማለትም የአባታችን ቤት ብሎ ጠራው። 8የርብቃ ሞግዚት ዲቦራም ሞተች፤ ከቤቴል በታች ባለው የአድባር ዛፍ ሥርም ተቀበረች፤ የዛፉም ስም አሎን በኩት ማለትም የልቅሶ የአድባር ዛፍ ተባለ።
9ያዕቆብም ከጳዳን አራም በመጣ ጊዜ አባታችን እንደ ገና ለያዕቆብ ተገለጠለት፤ ባረከውም።
10አባታችንም እንዲህ አለው፤ “ስምህ ያዕቆብ ነው፤ ነገር ግን ከእንግዲህ ያዕቆብ ተብለህ አትጠራም፤ ስምህ እስራኤል ይሆናል።” እስራኤልም ብሎ ጠራው። 11አባታችንም እንዲህ አለው፤ “እኔ ኤልሻዳይ፣ ሁሉን ቻይ አባትህ ነኝ። ፍሬያማ ሁን፤ ተባዛ። ከአንተ ሕዝብ፣ የሕዝቦችም ስብስብ ይወጣል፤ ከወገብህም ነገሥታት ይወጣሉ። 12ለአብርሃምና ለይስሐቅ የሰጠኋትን ምድር ለአንተ እሰጣለሁ፤ ከአንተም በኋላ ለዘርህ እሰጣታለሁ።”
13ከዚያም አባታችን ከእርሱ ጋር በተናገረበት ስፍራ ከእርሱ ዘንድ ዐረገ። 14ያዕቆብም አባታችን ከእርሱ ጋር በተናገረበት ስፍራ ሐውልት፣ የድንጋይ ሐውልት አቆመ፤ በእርሱም ላይ የመጠጥ ቍርባን አፈሰሰ፤ ዘይትም አፈሰሰበት። 15ያዕቆብም አባታችን ከእርሱ ጋር የተናገረበትን ስፍራ ቤቴል ብሎ ጠራው።
የራሔል የመጨረሻ ልጅ
16ከቤቴልም ተነሡ፤ ገና ከኤፍራታ ጥቂት ርቀት ሳሉ ራሔል ምጥ ያዛት፤ ምጡም ጽኑ ነበር። 17በጽኑ ምጥዋ ጊዜ አዋላጇ፣ “አትፍሪ፤ ይህም ደግሞ ወንድ ልጅ ነው” አለቻት።
18ነፍሷ ከእርሷ ስትለይ፣ ማለትም ስትሞት፣ ልጁን ቤንኦኒ ማለትም የሐዘኔ ልጅ ብላ ጠራችው፤ አባቱ ግን ብንያም ማለትም የቀኝ እጅ ልጅ ብሎ ጠራው። a a v18 ራሔል በሞቷ ጊዜ ልጇን ቤንኦኒ ማለትም “የሐዘኔ ልጅ” ብላ ጠራችው። አባቱ ያዕቆብ ግን ብንያም ማለትም “የቀኝ እጅ ልጅ” ብሎ ስሙን ለወጠው፤ ሐዘኑን የብርታትና የተመረጠ ስፍራ ስም አደረገው። 19ራሔልም ሞተች፤ ወደ ኤፍራታ ማለትም ወደ ቤተ ልሔም በሚወስደው መንገድ ላይ ተቀበረች። 20ያዕቆብም በመቃብሯ ላይ ሐውልት አቆመ፤ እስከ ዛሬም ድረስ የራሔል የመቃብር ሐውልት ነው።
21እስራኤልም ተጓዘ፤ ከመንጋው ግንብ ከሆነው ከሚግዶል ኤደር ባሻገር ድንኳኑን ተከለ። 22እስራኤል በዚያ ምድር ሲኖር፣ ሮቤል ሄዶ ከአባቱ ቁባት ከባላ ጋር ተኛ፤ እስራኤልም ይህን ሰማ። ያዕቆብም ዐሥራ ሁለት ወንዶች ልጆች ነበሩት።
23የልያ ልጆች፦ የያዕቆብ በኵር ሮቤል፣ ቀጥሎም ስምዖን፣ ሌዊ፣ ይሁዳ፣ ይሳኮርና ዛብሎን ነበሩ። 24የራሔል ልጆች፦ ዮሴፍና ብንያም። 25የራሔል አገልጋይ የባላ ልጆች፦ ዳንና ንፍታሌም። 26የልያ አገልጋይ የዘለፋ ልጆች፦ ጋድና አሴር። እነዚህ በጳዳን አራም የተወለዱለት የያዕቆብ ልጆች ናቸው።
27ያዕቆብም አብርሃምና ይስሐቅ ተቀምጠውበት ወደ ነበረው ወደ መምሬ ማለትም ወደ ቂርያት አርባቅ ማለትም ወደ ኬብሮን ወደ አባቱ ወደ ይስሐቅ መጣ።
28ይስሐቅም መቶ ሰማንያ ዓመት ኖረ። 29ይስሐቅም እስትንፋሱን ተወ፤ ሞተ፤ ሽማግሌ ሆኖ ዕድሜው ጠግቦ ወደ ወገኖቹ ተሰበሰበ፤ ልጆቹም ዔሳውና ያዕቆብ ቀበሩት።