ያንብቡ። ይቀበሉ። ይጠቁሙ።

♥ አስተያየቶች

ማርቆስ 1

መጽሐፍ

አባታችን መልእክተኛውን ይልካል

እጅግ አጭሩና ፈጣኑ ወንጌል፤ ኢየሱስን «ሊያገለግል ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት ያልመጣ» መከራ የተቀበለ አገልጋይ አድርጎ ይስለዋል።

ምዕራፍ 1።

የአባታችን ልጅ የሆነው የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መጀመሪያ። a a v1 አንዳንድ ጥንታዊ ቅጆች “የአባታችን ልጅ” የሚለውን አይዙም። በነቢዩ ኢሳይያስ እንደ ተጻፈ፦ “እነሆ፣ መንገድህን የሚያዘጋጀውን መልእክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ። በምድረ በዳ የሚጮኽ ድምፅ፦ ‘የጌታን መንገድ አዘጋጁ፣ ጐዳናዎቹን አቅኑ።’”

ዮሐንስ በምድረ በዳ እያጠመቀና ለኀጢአት ይቅርታ የንስሓ ጥምቀትን እየሰበከ ተገለጠ። የይሁዳ ምድር ሁሉና የኢየሩሳሌም ሰዎች ሁሉ ወደ እርሱ ይወጡ ነበር፤ ኀጢአታቸውንም እየተናዘዙ በዮርዳኖስ ወንዝ አጠመቃቸው። ዮሐንስ የግመል ጠጉር ለብሶ፣ በወገቡ ላይ የቈዳ ቀበቶ ታጥቆ ነበር፤ አንበጣና የበረሓ ማርም ይበላ ነበር። እንዲህም ብሎ አወጀ፤ “ከእኔ የሚበረታ ከእኔ በኋላ ይመጣል፤ ጐንበስ ብዬ የጫማውን ማሰሪያ ልፈታ እንኳ አይገባኝም። እኔ በውሃ አጠመቅኋችሁ፤ እርሱ ግን በመንፈስ ቅዱስ ያጠምቃችኋል።”

አብ በልጁ ላይ ተናገረ

በዚያ ወራት ኢየሱስ ከገሊላዋ ናዝሬት መጥቶ በዮርዳኖስ በዮሐንስ ተጠመቀ። ወዲያውም ከውሃው ሲወጣ ሰማያት ሲቀደዱና መንፈስ ቅዱስ እንደ ርግብ በእርሱ ላይ ሲወርድ አየ።

ከሰማይም ድምፅ መጣ፤ “አንተ የምወድህ ልጄ ነህ፤ በአንተ ደስ ይለኛል።”

ወዲያውም መንፈስ ቅዱስ ወደ ምድረ በዳ አወጣው። በምድረ በዳም አርባ ቀን ኖረ፤ በሰይጣን እየተፈተነ ከዱር አራዊት ጋር ነበረ፤ መላእክቱም ያገለግሉት ነበር።

ዮሐንስ ከታሰረ በኋላ ኢየሱስ የአባታችንን ወንጌል እየሰበከ ወደ ገሊላ መጣ፤

እንዲህም አለ፤ “ጊዜው ተፈጸመ፤ የአባታችንም መንግሥት ቀርቧል፤ ንስሓ ግቡ፤ በምሥራቹም እመኑ።”

ኢየሱስ የመጀመሪያ ደቀ መዛሙርቱን ጠራ

በገሊላ ባሕር ዳር ሲያልፍ ስምዖንና ወንድሙ እንድርያስ መረባቸውን ወደ ባሕር ሲጥሉ አየ፤ ዓሣ አጥማጆች ነበሩና።

ኢየሱስም፣ “ተከተሉኝ፤ ሰዎችን አጥማጆች አደርጋችኋለሁ” አላቸው።

ወዲያውም መረባቸውን ትተው ተከተሉት።

ጥቂት ወደ ፊት እልፍ ብሎ የዘብዴዎስን ልጅ ያዕቆብንና ወንድሙን ዮሐንስን በጀልባ ውስጥ መረባቸውን ሲጠግኑ አየ። ወዲያውም ጠራቸው፤ አባታቸውን ዘብዴዎስን ከተቀጠሩ ሠራተኞች ጋር በጀልባ ትተው ተከተሉት።

በጨለማ ላይ ሥልጣን

ወደ ቅፍርናሆም ገቡ። ወዲያውም በሰንበት ቀን ወደ ምኵራብ ገብቶ ማስተማር ጀመረ። በትምህርቱም ተገረሙ፤ እንደ ጸሐፍት ሳይሆን እንደ ባለ ሥልጣን ያስተምራቸው ነበርና። ወዲያውም በምኵራባቸው ርኩስ መንፈስ ያለበት ሰው ነበረ፤ እርሱም ጮኸ፤ አንተ የናዝሬቱ ኢየሱስ፣ ከእኛ ጋር ምን አለህ? ልታጠፋን መጣህን? ማን እንደ ሆንህ አውቃለሁ፤ የእግዚአብሔር ቅዱሱ ነህ!

ኢየሱስ ግን፣ “ዝም በል፤ ከእርሱም ውጣ!” ብሎ ገሠጸው።

ርኩሱም መንፈስ አንፈራፍሮት በታላቅ ድምፅ እየጮኸ ከእርሱ ወጣ። ሁሉም ተገረሙ፤ እርስ በርሳቸውም፣ “ይህ ምንድን ነው? በሥልጣን የተነገረ አዲስ ትምህርት ነው፤ ርኩሳን መናፍስትን እንኳ ያዝዛል፤ እነርሱም ይታዘዙታል!” ብለው ተጠያየቁ። ዝናውም ወዲያው በገሊላ ዙሪያ ባለው አገር ሁሉ በየስፍራው ተሰማ።

ፈውስ ወደ ስምዖን ቤት መጣ

ወዲያውም ከምኵራብ ወጥተው ከያዕቆብና ከዮሐንስ ጋር ወደ ስምዖንና ወደ እንድርያስ ቤት ገቡ። የስምዖን አማት በንዳድ ታማ ተኝታ ነበር፤ ወዲያውም ስለ እርሷ ነገሩት። ቀርቦም እጇን ይዞ አስነሣት፤ ንዳዱም ለቀቃት፤ እርሷም አገለገለቻቸው።

በዚያም ማታ ፀሓይ ስትጠልቅ፣ የታመሙትን ሁሉና በአጋንንት የተያዙትን ወደ እርሱ አመጡ። ከተማዪቱም ሁሉ በበሩ ዘንድ ተሰበሰበች። በልዩ ልዩ ደዌ የታመሙ ብዙዎችን ፈወሰ፤ ብዙ አጋንንትንም አወጣ፤ አጋንንቱም ስለሚያውቁት እንዲናገሩ አልፈቀደላቸውም።

ኢየሱስ ሊጸልይ ገለል አለ

ማለዳም ሳይነጋ ገና በጨለማ ተነሥቶ ወጣ፤ ወደ ምድረ በዳ ስፍራ ሄዶም በዚያ ጸለየ። ስምዖንና ከእርሱ ጋር የነበሩትም ፈለጉት፤ ባገኙትም ጊዜ፣ “ሰው ሁሉ ይፈልግሃል” አሉት።

እርሱም፣ “በዚያ ደግሞ እንድሰብክ ወደ ሌላ ስፍራ፣ ወደ አጎራባች መንደሮች እንሂድ፤ ለዚህ መጥቻለሁና” አላቸው።

በገሊላም ሁሉ በምኵራቦቻቸው እየሰበከና አጋንንትን እያወጣ ዞረ።

ለምጻሙ ነጻ ሆነ

ለምጽ ያለበት ሰው ወደ እርሱ መጥቶ ተንበርክኮ፣ “ብትወድስ ልታነጻኝ ትችላለህ” ብሎ ለመነው።

በጥልቅ ርኅራኄም ተነሣሥቶ እጁን ዘርግቶ ዳሰሰውና፣ “እወዳለሁ፤ ንጻ” አለው።

ወዲያውም ለምጹ ለቀቀው፤ ነጻም ሆነ። አጥብቆም አስጠንቅቆ ወዲያው አሰናበተው፤

እንዲህም አለው፤ “ለማንም እንዳትናገር ተጠንቀቅ፤ ነገር ግን ሂድና ራስህን ለካህኑ አሳይ፤ ለእነርሱም ምስክር እንዲሆን ስለ መንጻትህ ሙሴ ያዘዘውን አቅርብ።”

እርሱ ግን ወጥቶ ነገሩን በግልጥ እየሰበከና እያወራ ስለ ተናገረ፣ ኢየሱስ ዳግመኛ በግልጥ ወደ ከተማ መግባት አልቻለም፤ ነገር ግን በባዶ ስፍራዎች ይኖር ነበር። ሆኖም ሰዎች ከየስፍራው ወደ እርሱ ይመጡ ነበር።

A young man reading the Father's Heart Bible (FHB) print edition in a coffee shop አሁን በኅትመት ይገኛል

አስተያየቶች

ሐሳብ፣ ጥያቄ፣ ወይም ይህ ምዕራፍ በልብዎ ያነሣሣው ቃል — እዚህ ያካፍሉ። እያንዳንዱ አስተያየት ስምዎን በአስተዋጽኦ አበርካቾች ግድግዳ ላይ ያሰፍራል።

ማንበብ፣ ማዳመጥ፣ መቅዳትና ማጋራት ለሁሉም ክፍት ነው — መለያ አያስፈልግም። አስተያየት መስጠት፣ ቁጥሮችን ማድመቅና የደረሱበትን ቦታ ምልክት ማድረግ ከነጻ መለያ ጋራ ይመጣሉ፤ እያንዳንዱ አስተያየትም ስምዎን በአስተዋጽኦ አበርካቾች ግድግዳ ላይ ያሰፍራል።

ቤተሰቡን ይቀላቀሉ — በነጻ ነው →
  • እስካሁን ምንም አስተያየት የለም። ድምፅዎን በማሰማት የመጀመሪያው ይሁኑ።