ዳን የሚሰፍርበትን ስፍራ ይፈልጋል
ርስት የሌለው የዳን ሰላዮች የሚካን ቅጥር ካህን ከአብ ዘንድ ቃል እንዲጠይቅላቸው ይለምናሉ፤ መልካም ቃልም ያገኛሉ። ስድስት መቶ የታጠቁ ሰዎች ተመልሰው ቤተ ጣዖቱን ይዘርፋሉ፣ ለካህኑም የበለጠ ጉባኤ ይሰጡታል፤ እርሱም በደስታ ይሄዳል። ሰላማዊቱን ከተማ በሰይፍ ይመቱአታል፣ ምስሉንም ያቆማሉ።
18 1በዚያ ዘመን በእስራኤል ንጉሥ አልነበረም። የዳን ነገድ የሚሰፍርበትን ርስት ይፈልግ ነበር፤ ምክንያቱም እስከዚያ ቀን ድረስ በእስራኤል ነገዶች መካከል ርስት አልደረሳቸውም ነበር። 2የዳን ሰዎች ምድሪቱን እንዲሰልሉና እንዲመረምሩ ከጎሣቸው፣ ከጾርዓና ከኤሽታዖል አምስት ጀግኖችን ላኩ፤ “ሂዱ፣ ምድሪቱን መርምሩ” አሏቸው። ወደ ኤፍሬም ተራራማ አገር፣ ወደ ሚካ ቤት ደርሰው እዚያ አደሩ።
3ከሚካ ቤት አጠገብ ሳሉ የወጣቱን ሌዋዊ ድምፅ አወቁ፤ ስለዚህ ወደዚያ ዘወር ብለው፣ “ወደዚህ ማን አመጣህ? በዚህ ስፍራ ምን ታደርጋለህ? እዚህ ምን አለህ?” አሉት።
4እርሱም፣ “ሚካ እንዲህና እንዲህ አደረገልኝ፤ ቀጥሮኝ ካህኑ ሆንሁ” አላቸው።
5እነርሱም፣ “እባክህ አባታችንን ጠይቅልን፤ የምንሄድበት ጒዞ ይከናወን እንደ ሆነ እናውቅ ዘንድ” አሉት።
6ካህኑም፣ “በሰላም ሂዱ፤ የምትሄዱበት ጒዞ በአባታችን ጥበቃ ሥር ነው” አላቸው።
7አምስቱ ሰዎችም ወደ ላይስ ሄደው ሕዝቡን እንደ ሲዶናውያን በሰላም ሲኖር አዩ፤ ጸጥ ያሉና ተማምነው የሚኖሩ፣ በምድሩ ምንም የማይጎድላቸውና ባለጠግነት ያላቸው ነበሩ። ከሲዶናውያን የራቁ ነበሩ፤ ከማንም ጋራም ግንኙነት አልነበራቸውም። 8ወደ ዘመዶቻቸው ወደ ጾርዓና ወደ ኤሽታዖል በተመለሱ ጊዜ፣ “ምን አገኛችሁ?” ተባሉ።
9እነርሱም እንዲህ አሉ፤ “ተነሡ፣ እንውጋቸው! ምድሪቱን አይተናል፤ እጅግ መልካም ናት። ዝም ብላችሁ ትቀመጣላችሁን? ምድሪቱን ልትወርሱ ከመሄድ አትዘግዩ። 10በደረሳችሁ ጊዜ፣ ሰፊ በሆነ ምድር ላይ ጥርጣሬ የሌለውን ሕዝብ ታገኛላችሁ። አባታችን በእጃችሁ አሳልፎ ሰጥቷታል፤ በምድር ላይ ምንም የማይጎድልባት ስፍራ ናት።”
11ከዳን ጎሣ የሆኑ ስድስት መቶ ሰዎች የጦር መሣሪያ ታጥቀው ከጾርዓና ከኤሽታዖል ተነሡ። 12ወጥተውም በይሁዳ ባለችው በቂርያት ይዓሪም ሰፈሩ። ስለዚህ እስከ ዛሬ ድረስ ማሃኔ ዳን ተብሎ ይጠራል፤ ከቂርያት ይዓሪም በስተ ምዕራብ ይገኛል። 13ከዚያም ወደ ኤፍሬም ተራራማ አገር ተሻግረው ወደ ሚካ ቤት ደረሱ።
14የላይስን ምድር ሰልለው የመጡት አምስቱ ሰዎች ዘመዶቻቸውን እንዲህ አሉ፤ “በእነዚህ ቤቶች ውስጥ ኤፉድ፣ የቤት ጣዖታት፣ የተቀረጸ ምስልና የቀለጠ ምስል እንዳለ ታውቃላችሁን? እንግዲህ ምን ማድረግ እንዳለባችሁ ወስኑ።” 15ስለዚህ ዘወር ብለው ወደ ወጣቱ ሌዋዊ ቤት፣ ወደ ሚካ ቤት መጥተው ሰላምታ ሰጡት። 16የጦር መሣሪያ የታጠቁት ስድስት መቶ የዳን ሰዎች በበሩ መግቢያ ላይ ቆሙ። 17ምድሪቱን ሰልለው የመጡት አምስቱ ሰዎች ገብተው የተቀረጸውን ምስል፣ ኤፉዱን፣ የቤት ጣዖታቱንና የቀለጠውን ምስል ወሰዱ፤ ካህኑ ግን ከስድስት መቶ የታጠቁ ሰዎች ጋራ በበሩ መግቢያ ላይ ቆሞ ነበር።
18እነዚህ ሰዎች ወደ ሚካ ቤት ገብተው የተቀረጸውን ምስል፣ ኤፉዱን፣ የቤት ጣዖታቱንና የቀለጠውን ምስል በወሰዱ ጊዜ፣ ካህኑ፣ “ምን ታደርጋላችሁ?” ሲል ጠየቃቸው።
19እነርሱም እንዲህ አሉ፤ “ዝም በል! እጅህን በአፍህ ላይ አድርገህ ከእኛ ጋራ ና። ለእኛ አባትና ካህን ሁን። ለአንድ ሰው ቤት ካህን ትሆን ዘንድ፣ ወይስ በእስራኤል ለአንድ ነገድና ጎሣ ካህን ትሆን ዘንድ የትኛው ይሻልሃል?”
20የካህኑም ልብ ደስ አለው። ኤፉዱን፣ የቤት ጣዖታቱንና የተቀረጸውን ምስል ይዞ በሕዝቡ መካከል ሄደ። 21ከዚያም ዘወር ብለው ልጆቹን፣ ከብቶቹንና ንብረታቸውን በፊታቸው አድርገው ተጓዙ። 22ከሚካ ቤት በራቁ ጊዜ፣ በአጠገቡ የነበሩት ሰዎች ተጠርተው የዳንን ሰዎች ተከትለው ደረሱባቸው። 23የዳንንም ሰዎች ጮኹባቸው፤ እነርሱም ዘወር ብለው ሚካን፣ “ሰዎችህን እንዲህ እየጠራህ ያስጨነቀህ ምንድን ነው?” አሉት።
24እርሱም፣ “የሠራኋቸውን አማልክትና ካህኑን ወስዳችሁ ሄዳችሁ። ታዲያ የቀረኝ ምንድን ነው? እንዴትስ፣ ‘ምን ሆንህ?’ ብላችሁ ትጠይቁኛላችሁ?” አለ።
25የዳንም ሰዎች፣ “ድምፅህ በእኛ መካከል አይሰማ፤ አለዚያ የተቈጡ ሰዎች ይወጉሃል፤ አንተም ሕይወትህን፣ የቤተ ሰብህንም ሕይወት ታጣለህ” አሉት።
26የዳንም ሰዎች መንገዳቸውን ቀጠሉ፤ ሚካም ከእርሱ ይልቅ እንደ በረቱ ባየ ጊዜ ዘወር ብሎ ወደ ቤቱ ተመለሰ። 27ሚካ የሠራውን ነገርና ካህኑን ይዘው ወደ ላይስ መጡ፤ ጸጥ ያሉ፣ ጥርጣሬ የሌላቸውን ሕዝብ በሰይፍ ስለት መትተው ከተማይቱን በእሳት አቃጠሉ። 28ከተማይቱ ከሲዶን ርቃ ስለ ነበረችና ከማንም ጋራ ግንኙነት ስላልነበራት የሚያድናቸው ማንም አልነበረም። በቤተ ርሖብ ሸለቆ ውስጥ ትገኝ ነበር። የዳንም ሰዎች ከተማይቱን መልሰው ሠርተው እዚያ ሰፈሩ። 29ከተማይቱንም በእስራኤል ልጅ በአባታቸው በዳን ስም ዳን ብለው ሰየሟት፤ ከተማይቱ ግን ቀድሞ ላይስ ትባል ነበር። 30የዳንም ሰዎች የተቀረጸውን ምስል ለራሳቸው አቆሙ። የሙሴ ልጅ የሆነው የጌርሶም ልጅ ዮናታንና ልጆቹ ምድሪቱ እስከ ተማረከችበት ቀን ድረስ ለዳን ነገድ ካህናት ነበሩ። 31የአባታችን ቤት በሴሎ በነበረበት ዘመን ሁሉ፣ ሚካ የሠራውን የተቀረጸ ምስል ለራሳቸው አቆሙ።