ያንብቡ። ይቀበሉ። ይጠቁሙ።

♥ አስተያየቶች

ምሳሌ 24

መጽሐፍ

ጥበብ ቤትን ትሠራለች

መገንባትና ማዳን። ቤት በጥበብ ይሠራል፤ ጻድቅ ሰባት ጊዜ ወድቆ ይነሣል። በጠላት ውድቀት መደሰትን ይከለክላል፤ ሰዎች ወደ ሞት ሲነዱም «አላወቅንም» የሚለውን ምክንያት አይቀበልም። በአረም የታነቀ የወይን ቦታ ያስተምረዋል።

ምዕራፍ 24።

ክፉ ሰዎችን አትቅና፤ ከእነርሱም ጋራ ለመሆን አትመኝ፤ ልባቸው ግፍን ያውጠነጥናልና፤ ከንፈሮቻቸውም ጥፋትን ይናገራሉ።

ቤት በጥበብ ይሠራል፤ በማስተዋልም ይጸናል፤ ክፍሎቹም በዕውቀት ውድና ደስ በሚያሰኝ ሀብት ሁሉ ይሞላሉ።

ጠቢብ ሰው ብርታት የተሞላ ነው፤ ዐዋቂ ሰውም ኀይሉን ያበዛል፤ ጦርነትህን በጥበብ መሪነት ትዋጋለህና፤ ድልም በብዙ አማካሪዎች ይገኛል።

ጥበብ ለተላላ ሰው በጣም ከፍ ያለች ናት፤ በበሩም ዘንድ የሚናገረው የለውም። ክፉ ለማድረግ የሚያስብ ሁሉ ተንኰለኛ ይባላል። የተላላ ተንኰል ኀጢአት ነው፤ ፌዘኛውም ለሰዎች አስጸያፊ ነው።

በመከራ ቀን ብትዝል፣ ኀይልህ ትንሽ ነው። ወደ ሞት የሚወሰዱትን አድን፤ ወደ መታረድም የሚንገዳገዱትን ከልክል። “እነሆ፣ ይህን አላወቅንም” ብትል፣ ልብን የሚመዝነው አያስተውለውምን? ነፍስህንም የሚጠብቀው አያውቀውምን? ለእያንዳንዱም ደግሞ እንደ ሥራው አይከፍለውምን?

ልጄ ሆይ፣ ማር ብላ፣ መልካም ነውና፤ ከወለላም የሚንጠባጠበው ለአንደበትህ ጣፋጭ ነው። ጥበብም ለነፍስህ እንደዚሁ እንደ ሆነች እወቅ፤ ብታገኛትም የወደፊት ተስፋ አለ፤ ተስፋህም አይቋረጥም።

አንተ ክፉ ሰው ሆይ፣ በጻድቁ መኖሪያ ላይ አታድባ፤ ማረፊያ ስፍራውንም አታጥፋ፤ ጻድቅ ሰባት ጊዜ ቢወድቅም እንደ ገና ይነሣልና፤ ክፉዎች ግን በጥፋት ይሰናከላሉ።

ጠላትህ በሚወድቅበት ጊዜ ደስ አይበልህ፤ በሚሰናከልበትም ጊዜ ልብህ ደስ አይበለው፤ አባታችን አይቶ እንዳይከፋውና ቍጣውንም ከእርሱ ላይ እንዳያዞር።

ክፉ አድራጊዎችን በማሰብ አትጨነቅ፤ ክፉዎችንም አትቅና፤ ክፉ ሰው የወደፊት ተስፋ የለውምና፤ የክፉዎች መብራት ይጠፋል።

ልጄ ሆይ፣ አባታችንንና ንጉሡን ፍራ፤ በእነርሱም ላይ ከሚያምፁ ጋራ አትተባበር፤ መቅሠፍታቸው በድንገት ይነሣልና፤ ሁለቱም ሊያመጡ የሚችሉትን ጥፋት ማን ያውቃል?

ያለ አድልዎ የሚሰጥ ፍርድ

እነዚህም ደግሞ የጠቢባን ቃሎች ናቸው፦ በፍርድ አድልዎ ማድረግ መልካም አይደለም። በደለኛውን፣ “ንጹሕ ነህ” የሚለውን ሁሉ፣ አሕዛብ ይረግሙታል፤ ሕዝቦችም ይዘልፉታል፤ በደለኛውን ለሚወቅሱ ግን መልካም ይሆንላቸዋል፤ የበዛ በረከትም ይመጣባቸዋል። ቅን መልስ በከንፈር እንደ መሳም ነው። በውጭ ያለውን ሥራህን አዘጋጅ፤ እርሻህንም አመቻች፤ ከዚያም በኋላ ቤትህን ሥራ። በባልንጀራህ ላይ ያለ ምክንያት ምስክር አትሁን፤ በከንፈሮችህስ ታታልላለህን? “እርሱ ባደረገብኝ ልክ እኔም እንዲሁ አደርግበታለሁ፤ ሰውየውንም እንዳደረገው እከፍለዋለሁ” አትበል። በሰነፍ ሰው እርሻ አጠገብ፣ ዐእምሮ በጎደለው ሰው ወይን ተክል አጠገብ ዐለፍሁ፤ እነሆም፣ ሁሉ በእሾህ በቅሎ ነበር፤ ምድሩም በአረም ተሸፍኖ ነበር፤ የድንጋይ ቅጥሩም ፈርሶ ነበር። ከዚያም ተመለከትሁና በልቤ ያዝሁት፤ አይቼም ትምህርት ተቀበልሁ። ጥቂት እንቅልፍ፣ ጥቂት እረፍት፣ ለማረፍ እጅን ጥቂት ማጣመር፣ ድኽነትም እንደ ወንበዴ ይመጣብሃል፤ ችጋርም እንደ ታጠቀ ሰው ይመጣብሃል።

A young man reading the Father's Heart Bible (FHB) print edition in a coffee shop አሁን በኅትመት ይገኛል

አስተያየቶች

ሐሳብ፣ ጥያቄ፣ ወይም ይህ ምዕራፍ በልብዎ ያነሣሣው ቃል — እዚህ ያካፍሉ። እያንዳንዱ አስተያየት ስምዎን በአስተዋጽኦ አበርካቾች ግድግዳ ላይ ያሰፍራል።

ማንበብ፣ ማዳመጥ፣ መቅዳትና ማጋራት ለሁሉም ክፍት ነው — መለያ አያስፈልግም። አስተያየት መስጠት፣ ቁጥሮችን ማድመቅና የደረሱበትን ቦታ ምልክት ማድረግ ከነጻ መለያ ጋራ ይመጣሉ፤ እያንዳንዱ አስተያየትም ስምዎን በአስተዋጽኦ አበርካቾች ግድግዳ ላይ ያሰፍራል።

ቤተሰቡን ይቀላቀሉ — በነጻ ነው →
  • እስካሁን ምንም አስተያየት የለም። ድምፅዎን በማሰማት የመጀመሪያው ይሁኑ።