የአባታችን ኪዳን ከዳዊት ጋር
ዳዊት ለአብ ቤት ሊሠራ ይፈልጋል፤ ናታንም ከእርሱ ሳይሰማ ይስማማል። መልሱ ግን ነገሩን ይገለብጠዋል፤ አብ ለአንተ ቤት ይሠራልሃል፤ ልጅህም ለእኔ ቤት ይሠራል። ዳዊት ሄዶ በፊቱ ይቀመጣል፤ ይህ ሁሉ እርሱን የሚመለከት በመሆኑ ልቡ ይቀልጣል።
17 1ዳዊት በቤቱ ከተቀመጠ በኋላ፣ ነቢዩን ናታንን እንዲህ አለው፤ “እነሆ፣ እኔ በዝግባ ቤት እኖራለሁ፤ የአባታችን ኪዳን ታቦት ግን በድንኳን መጋረጃ ሥር ይኖራል።”
2ናታንም ዳዊትን እንዲህ ብሎ መለሰ፤ “በልብህ ያለውን ሁሉ አድርግ፤ አባታችን ከአንተ ጋር ነውና።”
3በዚያች ሌሊት ግን የአባታችን ቃል ወደ ናታን እንዲህ ሲል መጣ፤
4ሂድና ባሪያዬን ዳዊትን እንዲህ በለው፤ “አባትህ እንዲህ ይላል፤ የምኖርበትን ቤት የምትሠራልኝ አንተ አይደለህም።” 5እስራኤልን ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በቤት ውስጥ አልኖርሁም፤ ከድንኳን ወደ ድንኳን፣ ከማደሪያ ወደ ማደሪያ ስዘዋወር ኖርሁ።
6ከእስራኤል ሁሉ ጋር በተዘዋወርሁበት ስፍራ ሁሉ፣ ሕዝቤን እንዲጠብቁ ካዘዝኋቸው ከእስራኤል ፈራጆች ለአንዱ፣ ‘ለምን የዝግባ ቤት አልሠራችሁልኝም?’ ብዬ አንዳች ቃል ተናግሬ አውቃለሁን?
7ስለዚህ ባሪያዬን ዳዊትን እንዲህ በለው፤ “የሰማይ ሠራዊት አባት እንዲህ ይላል፤ በሕዝቤ በእስራኤል ላይ ገዥ እንድትሆን፣ ከግጦሽ፣ መንጋውን ከመከተል ወሰድሁህ። 8በሄድህበት ስፍራ ሁሉ ከአንተ ጋር ነበርሁ፤ ጠላቶችህንም ሁሉ ከፊትህ አጠፋሁ። አሁንም ስምህን በምድር ላይ እንዳሉት ታላላቅ ሰዎች ስም አደርገዋለሁ። 9ለሕዝቤ ለእስራኤል ስፍራ እመድባለሁ፤ በዚያም እተክላቸዋለሁ፤ ዳግመኛም ሳይታወኩ በገዛ መኖሪያቸው ይኖራሉ። ክፉ ሰዎችም እንደ ቀድሞው ከእንግዲህ አያስጨንቋቸውም፤ 10በሕዝቤ በእስራኤል ላይ ፈራጆችን ከሾምሁበት ጊዜ ጀምሮ፣ ጠላቶችህን ሁሉ አስገዛለሁ። እነግርሃለሁ፤ አባትህ ቤት ይሠራልሃል። 11ዘመንህ አልቆ ከአባቶችህ ጋር ለመሆን በሄድህ ጊዜ፣ ከአንተ በኋላ ዘርህን፣ ከወንዶች ልጆችህ አንዱን አስነሣለሁ፤ መንግሥቱንም አጸናለሁ። 12ቤት የሚሠራልኝ እርሱ ነው፤ ዙፋኑንም ለዘላለም አጸናለሁ። 13እኔ አባቱ እሆናለሁ፤ እርሱም ልጄ ይሆናል። ከአንተ በፊት ከነበረው እንዳስወገድሁት፣ ከእርሱ የኪዳኔን ፍቅር አላስወግድም። 14በቤቴና በመንግሥቴ ላይ ለዘላለም እሾመዋለሁ፤ ዙፋኑም ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።”
15ናታንም ይህን ቃል ሁሉ፣ ይህንም ራእይ በሙሉ ለዳዊት ነገረው።
ዳዊት በአባታችን ፊት በመደነቅ ተቀመጠ
16ከዚያም ንጉሡ ዳዊት ገብቶ በአባታችን ፊት ተቀመጠ፤ እንዲህም አለ፤ “አባቴ ሆይ፣ እስከዚህ ድረስ ያደረስኸኝ፣ እኔ ማን ነኝ? ቤቴስ ምንድን ነው? 17አባቴ ሆይ፣ ይህም በዐይንህ ፊት እንደ ትንሽ ነገር ሆነ፤ ስለ ባሪያህ ቤት ወደ ሩቁ ዘመን እስኪደርስ ድረስ ተናገርህ፤ አባቴ ሆይ፣ እንደ ሰዎች ሁሉ ታላቅ አድርገህ አየኸኝ። 18ባሪያህን ስለ ማክበርህ ዳዊት ከዚህ በላይ ምን ሊልህ ይችላል? አንተ ባሪያህን ታውቀዋለህና። 19አባቴ ሆይ፣ ስለ ባሪያህና እንደ ገዛ ልብህ፣ ይህን ታላቅ ነገር ሁሉ አድርገሃል፤ ይህን ታላቅ ተስፋ ሁሉ ገልጠሃል። 20አባቴ ሆይ፣ በጆሮአችን እንደ ሰማነው ሁሉ፣ አንተን የሚመስል የለም፤ ከአንተ በቀር ሌላ አባት የለም። 21ከግብፅ የተቤዠኸውን ሕዝብህን ከፊት አሕዛብን እያባረርህ፣ በታላቅና በሚያስፈራ ሥራ ለራስህ ስም እያደረግህ፣ አባታችን ለራሱ ሕዝብ ሊያደርገው ሊቤዠው የሄደ፣ በምድር ላይ ያለ አንድ ሕዝብ፣ እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ያለ ማን ነው? 22ሕዝብህን እስራኤልን ለዘላለም የራስህ አደረግህ፤ አንተም አባቴ ሆይ፣ አባታቸው ሆንህ። 23አሁንም አባቴ ሆይ፣ ስለ ባሪያህና ስለ ቤቱ የተናገርኸው ቃል ለዘላለም ይጽና፤ እንደ ተናገርህም አድርግ። 24ይጽና፤ ስምህም ለዘላለም ይልቅ፤ ስለዚህም ‘የሰማይ ሠራዊት አባት በእስራኤል ላይ አባታችን ነው’ ይባላል። የባሪያህም የዳዊት ቤት በፊትህ ይጽና። 25አባቴ ሆይ፣ ቤት እንደምትሠራለት ለባሪያህ ገልጠህለታልና፤ ስለዚህ ባሪያህ በፊትህ ለመጸለይ ድፍረትን አገኘ። 26አሁንም አባቴ ሆይ፣ አንተ አባታችን ነህ፤ ይህን መልካም ነገር ለባሪያህ ተስፋ ሰጥተሃል። 27አሁንም የባሪያህን ቤት ልትባርክ ወደድህ፤ ስለዚህ በፊትህ ለዘላለም ይኖራል፤ አባቴ ሆይ፣ አንተ ባርከኸዋልና፤ ለዘላለምም የተባረከ ነው።”