አባታችን ለሙሴ ተናገረ
ርኩሳን ከሰፈሩ ውጭ ይወጣሉ፤ በደለኞች ሙሉውን ከአምስተኛው ጋር መመለስ አለባቸው፤ የባል ቅናትም ከገዛ እጁ ተወስዶ በጥርጣሬና በግል በቀል ሳይሆን በመሐላና በመራራ ውሃ በአብ ፊት ይፈታል።
5 1አባታችን ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረ፦
2“እስራኤላውያን የቈዳ በሽታ ያለበትን ሁሉ፣ ፈሳሽ ያለበትን ሁሉ፣ በሬሳ የረከሰውን ሁሉ ከሰፈር እንዲያስወጡ እዘዛቸው። 3ወንድም ሆነ ሴት፣ ከሰፈር ውጭ አስወጣቸው፤ እኔ በመካከላቸው የምኖርበትን ሰፈራቸውን እንዳያረክሱ።”
4እስራኤላውያንም እንዲሁ አደረጉ፤ ከሰፈር ውጭ አስወጧቸው፤ አባታችን ሙሴን እንዳዘዘው፣ እስራኤላውያን እንዲሁ አደረጉ።
ኀጢአትን መናዘዝና ካሳ መክፈል
5ከዚያም አባታችን ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረ፦
6“ለእስራኤል ሕዝብ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ ወንድ ወይም ሴት ሰዎች ከሚሠሩት ኀጢአት አንዱን ሠርቶ ቢከዳኝ፣ ያ ሰው በደለኛ ነው። 7የሠሩትን ኀጢአት መናዘዝ አለባቸው፤ ስለ በደሉ ሙሉ ካሳ ይክፈሉ፤ አንድ አምስተኛውን ጨምረው ለበደሉት ሰው ይስጡ። 8ነገር ግን ያ ሰው ካሳውን የሚቀበል ዘመድ ከሌለው፣ ካሳው የእኔ ስለሆነ ለካህኑ ይሰጣል፤ ከዚህም ጋራ በደለኛውን ለማስተስረይ የሚቀርበው አውራ በግ ይጨመራል። 9እስራኤላውያን ከሚያቀርቡት ከተቀደሱት ስጦታዎች ሁሉ ወደ ካህኑ የሚመጣው መባ ሁሉ የእርሱ ነው። 10የእያንዳንዱ ሰው የተቀደሰ ስጦታ የራሱ ሆኖ ይኖራል፤ ሰው ለካህኑ የሚሰጠው ግን የካህኑ ነው።”
የቅንዓት ፈተና
11ከዚያም አባታችን ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረ፦
12“ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ የማንም ሰው ሚስት ብትስትና ለባሏ ታማኝ ባትሆን፣ 13ሌላ ሰው ከእርሷ ጋራ ተኝቶ ይህም ከባሏ ተሰውሮ፣ ምንም እንኳ ብትረክስ ሳትታወቅ ብትቀር፣ የሚመሰክርባትም ባይኖር፣ በድርጊቱም ላይ ባትያዝ፣ 14የቅንዓት መንፈስ ባልዋን አድሮበት በረከሰችው ሚስቱ ላይ ቢቀናባት፣ ወይም የቅንዓት መንፈስ አድሮበት ባትረክስም እንኳ ቢቀናባት፣ 15ሰውዬው ሚስቱን ከቍርባንዋ ጋራ ወደ ካህኑ ያምጣ፤ ቍርባንዋም ሁለት ሊትር ያህል የገብስ ዱቄት ይሁን። ይህ የቅንዓት የእህል ቍርባን፣ በደልን የሚያስታውስ የመታሰቢያ ቍርባን ስለሆነ፣ ዘይት አያፍስስበት፤ ዕጣንም አያድርግበት። 16ካህኑም ያቅርባት፤ በአባታችንም ፊት ያቁማት። 17ካህኑም በሸክላ ዕቃ ውስጥ የተቀደሰ ውሃ ይውሰድ፤ ከማደሪያው ድንኳን ወለል ላይ ዐፈር ወስዶ በውሃው ውስጥ ይጨምር። a a v17 ይህ የመራራ ውሃ ሥርዐት ከእግዚአብሔር የሆነ የፈተና ፍርድ ነበር፤ ሴቲቱ በደለኛ ብትሆን በሥጋዋ ላይ ጉዳት ይደርስባታል፤ ንጹሕ ብትሆን ግን ምንም ጉዳት አይደርስባትም። 18ካህኑም ሴቲቱን በአባታችን ፊት ያቁማት፤ ጠጕሯንም ይፍታ፤ የመታሰቢያውን የእህል ቍርባን ማለትም የቅንዓቱን ቍርባን በእጆቿ ላይ ያድርግ፤ እርሱም መራራውን መርገምን የሚያመጣ ውሃ በእጁ ይይዝ። 19ካህኑም እንዲህ ብሎ ያምላት፤ ‘ማንም ሰው ከአንቺ ጋራ ካልተኛ፣ አንቺም ሳትስቺ በባልሽ ሥልጣን ሥር ሳትረክሺ ብትሆኚ፣ መርገምን ከሚያመጣው ከዚህ መራራ ውሃ ንጽሕት ሁኚ። 20ነገር ግን በባልሽ ሥር ሳለሽ ስተሽ ብትረክሺ፣ ከባልሽም ሌላ ሰው ከአንቺ ጋራ ተኝቶ ቢሆን፣’ 21ካህኑም ሴቲቱን በዚህ የመርገም መሐላ እንዲህ ብሎ ያስራት፤ አብ ጭንሽን አድርቆ ሆድሽን ባስነፋ ጊዜ፣ በሕዝብሽ መካከል ለመርገምና ለውርደት ያድርግሽ፤ 22መርገምን የሚያመጣው ይህ ውሃ ወደ ሰውነትሽ ገብቶ ሆድሽን ያስነፋ፤ ጭንሽንም ያድርቅ። ሴቲቱም፣ ‘አሜን፣ አሜን’ ትበል።
23“ከዚያም ካህኑ እነዚህን መርገሞች በጥቅልል ጽፎ ወደ መራራው ውሃ ውስጥ ያጥባቸው። 24ሴቲቱንም መራራውን የመርገም ውሃ ያጠጣት፤ የመርገሙም ውሃ ገብቶባት መራራ ሥቃይ ያመጣባታል። 25ካህኑም የቅንዓቱን የእህል ቍርባን ከእጇ ወስዶ በአባታችን ፊት ያወዛውዘው፤ ወደ መሠውያውም ያቅርበው። 26ካህኑም ከእህሉ ቍርባን ማለትም ከመታሰቢያው እፍኝ ሞልቶ ወስዶ በመሠውያው ላይ ያቃጥለው፤ ከዚያም ሴቲቱን ውሃውን ያጠጣት። 27ውሃውንም ካጠጣት በኋላ፣ ራሷን አርክሳ ባሏን ከድታ ከሆነ፣ መርገምን የሚያመጣው ውሃ ገብቶባት መራራ ሥቃይ ያመጣባታል፤ ሆዷ ይነፋል፤ ጭኗም ይደርቃል፤ እርሷም በሕዝቧ መካከል የመርገም ምሳሌ ትሆናለች። 28ሴቲቱ ግን ራሷን ያላረከሰችና ንጹሕ ከሆነች፣ ነጻ ትሆናለች፤ ልጆችንም ትፀንሳለች።
29“የቅንዓት ሕግ ይህ ነው፤ በባሏ ሥር ያለች ሚስት ስታ ራሷን ባረከሰች ጊዜ፣ 30ወይም የቅንዓት መንፈስ ሰውን ይዞት በሚስቱ ላይ በቀናባት ጊዜ፣ ሚስቱን በአባታችን ፊት ያቁም፤ ካህኑም ይህን ሕግ ሁሉ በእርሷ ላይ ያድርግ። 31ባሉም ከበደል ነጻ ይሆናል፤ ሴቲቱ ግን የራሷን ኀጢአት ትሸከማለች።”