ዐግ ሊዋጋ ወጣ
የባሳን ንጉሥ ዐግና ስድሳ የተመሸጉ ከተሞቹ እንደ ሴዎን ይወድቃሉ፤ አብ የሰጠው ምድርም ለሮቤል፣ ለጋድና ለምናሴ እኩሌታ ነገድ ይከፋፈላል፤ ተዋጊዎቻቸው ግን አሁንም ታጥቀው ከወንድሞቻቸው ፊት መሻገር አለባቸው። ሙሴ ምድሪቱን ለማየት ይለምናል፤ ወደ ፈስጋም እንዲወጣ ይላካል።
3 1ዞረን ወደ ባሳን የሚወስደውን መንገድ ያዝን፤ የባሳንም ንጉሥ ዐግ ከሕዝቡ ሁሉ ጋራ በኤድራይ ሊዋጋን ወጣ።
2አባታችንም እንዲህ አለኝ፤ “አትፍራው፤ እርሱንና ሕዝቡን ሁሉ ምድሩንም በእጅህ ሰጥቼሃለሁና፤ በሐሴቦን ይኖር የነበረውን የአሞራውያንን ንጉሥ ሴዎንን እንዳደረግህበት እንዲሁ አድርግበት።”
3እንዲሁም አባታችን የባሳንን ንጉሥ ዐግን ሕዝቡንም ሁሉ በእጃችን ሰጠን፤ አንድም ሳያስቀር እስኪጠፉ ድረስ መታናቸው። 4በዚያም ጊዜ ከተሞቹን ሁሉ ያዝን፤ ያልያዝነው አንድም ከተማ አልቀረም፤ ስድሳውን ከተማ ሁሉ፣ የአርጎብን አውራጃ ሁሉ፣ በባሳን የነበረውን የዐግን መንግሥት ያዝን። 5እነዚህ ሁሉ ከፍ ባለ ቅጥርና በተቈለፈ በር የተጠበቁ ከተሞች ነበሩ፤ ከዚህም ሌላ ቅጥር የሌላቸው እጅግ ብዙ መንደሮች ነበሩ። 6የሐሴቦንን ንጉሥ ሴዎንን እንዳደረግን እነርሱን ለጥፋት ለየናቸው፤ ከተማውን ሁሉ፣ ወንዶቹን፣ ሴቶቹንና ሕፃናቱን ለጥፋት ለየን። 7እንስሳውን ሁሉና የከተሞቹን ብዝበዛ ግን ለራሳችን ማርከን ወሰድን። 8በዚያም ጊዜ ከዮርዳኖስ ማዶ ከነበሩት ከእነዚህ ከሁለቱ የአሞራውያን ነገሥታት ከአርኖን ሸለቆ አንሥቶ እስከ አርሞንኤም ተራራ ድረስ ያለውን ምድር ወሰድን። 9(አርሞንኤምን ሲዶናውያን ሲርዮን ይሉታል፤ አሞራውያን ግን ሴኒር ይሉታል)፤ 10የአምባውን ከተሞች ሁሉ፣ ገለዓድን ሁሉ፣ እስከ ሳሌካና እስከ ኤድራይ ድረስ ያለውን ባሳንን ሁሉ፣ በባሳን የነበሩትን የዐግን የመንግሥት ከተሞች ወሰድን። 11(ከቀሩት ከሬፋውያን የባሳን ንጉሥ ዐግ ብቻ ቀርቶ ነበር፤ አልጋውም የብረት አልጋ ነበር፤ በአሞናውያን ረባት ያለው አይደለምን? ርዝመቱ ዐሥራ ሦስት ጫማ ተኩል፣ ስፋቱም ስድስት ጫማ ያህል ነበር።)። a a v11 ሬፋውያን ቀድሞ በከነዓን ይኖሩ የነበሩ የግዙፍ ተዋጊዎች አፈ ታሪካዊ ወገን ነበሩ።
ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ የተከፈለው ምድር
12በዚያን ጊዜ የወሰድነው ይህ ምድር ይህ ነው፤ በአርኖን ሸለቆ ዳር ካለችው ከአሮዔር አንሥቶ ያለውን፣ ከገለዓድም ተራራማ አገር እኩሌታውንና ከተሞቹን ለሮቤላውያንና ለጋዳውያን ሰጠኋቸው። 13የቀረውን የገለዓድ ክፍልና የዐግ መንግሥት የነበረችውን ባሳንን ሁሉ ለምናሴ እኩሌታ ነገድ ሰጠኋቸው፤ የአርጎብን አውራጃ ሁሉ ሰጠኋቸው። (ያ የባሳን ክፍል ሁሉ የሬፋውያን ምድር ይባል ነበር። 14የምናሴ ልጅ ኢያዕር እስከ ጌሹራውያንና እስከ መዓካውያን ድንበር ድረስ የአርጎብን አውራጃ ሁሉ ወሰደ፤ ባሳንንም እስከ ዛሬ ድረስ በስሙ ሐዎት ኢያዕር ብሎ ሰየማት።)። 15ለማኪርም ገለዓድን ሰጠሁት። 16ለሮቤላውያንና ለጋዳውያን ከገለዓድ አንሥቶ እስከ አርኖን ሸለቆ ድረስ—የሸለቆው መካከል ድንበር ሆኖ—እስከ ያቦቅ ወንዝ የአሞናውያን ድንበር ድረስ ያለውን ሰጠኋቸው። 17ደግሞም ዓረባን፣ ዮርዳኖስ ድንበሩ ሆኖ፣ ከኪኔሬት አንሥቶ እስከ ዓረባ ባሕር (የሙት ባሕር) ድረስ፣ ከፈስጋ ተዳፋት በታች፣ ወደ ምሥራቅ ያለውን ሰጠኋቸው።
18በዚያም ጊዜ እንዲህ ብዬ አዘዝኋችሁ፤ “አባታችሁ ይህችን ምድር ትወርሷት ዘንድ ሰጥቷችኋል፤ ተዋጊዎቻችሁ ሁሉ የጦር ዕቃ ይዘው ከወንድሞቻችሁ ከእስራኤላውያን ፊት ተሻግረው ይሂዱ። 19ሚስቶቻችሁ፣ ልጆቻችሁና እንስሶቻችሁ ብቻ—ብዙ እንስሳ እንዳላችሁ ዐውቃለሁ—በሰጠኋችሁ ከተሞች ይቀመጡ፤ 20አባታችን እንደ እናንተ ለወንድሞቻችሁ ዕረፍት እስኪሰጥ፣ እነርሱም አባታችሁ ከዮርዳኖስ ማዶ የሚሰጣቸውን ምድር እስኪወርሱ ድረስ፤ ከዚያም እያንዳንዳችሁ ወደ ሰጠኋችሁ ርስት ትመለሳላችሁ።”
21በዚያም ጊዜ ኢያሱን እንዲህ ብዬ አዘዝኩት፤ “አባትህ በእነዚህ በሁለቱ ነገሥታት ያደረገውን ሁሉ ዐይኖችህ አይተዋል፤ አባትህ ወደ ምትሻገርባቸው መንግሥታት ሁሉ እንዲሁ ያደርጋል።
አትፍራ፤ እርሱ ስለ አንተ ይዋጋል
22አትፍራቸው፤ አባትህ ራሱ ስለ አንተ ይዋጋልና።”
23በዚያም ጊዜ አባታችንን እንዲህ ብዬ ለመንኩት፤ 24“ጌታ አባቴ ሆይ፣ ታላቅነትህንና ብርቱ እጅህን ለባሪያህ ማሳየት ጀምረሃል፤ በሰማይ ወይም በምድር እንዳንተ ሥራና ኀያል ተግባር ሊያደርግ የሚችል የትኛው አምላክ ነው? 25እባክህ ተሻግሬ ከዮርዳኖስ ማዶ ያለውን መልካሙን ምድር፣ ይህን መልካም ተራራማ አገርና ሊባኖስን አይ ዘንድ ፍቀድልኝ።”
26አባታችን ግን ስለ እናንተ ተቈጣኝ፤ አልሰማኝም፤ አባታችንም እንዲህ አለኝ፤ “ይበቃሃል! ከእንግዲህ ስለዚህ ነገር አትናገረኝ። 27ወደ ፈስጋ ጫፍ ውጣ፤ ዐይኖችህንም ወደ ምዕራብ፣ ወደ ሰሜን፣ ወደ ደቡብና ወደ ምሥራቅ አንሥተህ በዐይኖችህ ተመልከት፤ ይህን ዮርዳኖስ አትሻገረውምና። 28ነገር ግን ኢያሱን ሹመው፤ አበረታታው፤ አጠንክረውም፤ እርሱ ከዚህ ሕዝብ ፊት ይሻገራልና፤ የምታየውንም ምድር ያወርሳቸዋልና።”
29እንዲሁም በቤትፌጎር ትይዩ ባለው ሸለቆ ተቀመጥን።