አብ ማሰሮውን ይሰብረዋል
በአባታችን ቃል ኤርምያስ ሽማግሌዎችን ልጆች ይቃጠሉበት ወደ ነበረው ሸለቆ ይዞ ይወጣል፤ የዕርድ ሸለቆ ብሎ ይሰይመዋል፤ በፊታቸውም የሸክላ ማሰሮ ይሰብራል። እንደ ሸክላ ሠሪው ማሰሮ ሳይሆን ይህ እንደገና ሊሠራ አይችልም። ቃሉንም ይዞ ወደ ቤተ መቅደሱ አደባባይ ይመለሳል።
19 1አባታችን እንዲህ አለ፦ ሄደህ የሸክላ ሠሪ ማሰሮ ግዛ፤ ከሕዝቡ ሽማግሌዎችና ከካህናቱ ሽማግሌዎች አንዳንዶቹን ይዘህ፣ 2በሸክላ ስብርባሪ በር መግቢያ ወዳለው ወደ ቤንሂኖም ሸለቆ ውጣ፤ የምነግርህንም ቃል በዚያ ዐውጅ። a a v2 ሸክላ ስብርባሪ የተሰበረ የሸክላ ዕቃ ፍንጥርጣሪ ነው፤ በሩም በአቅራቢያው ይጣሉ በነበሩት ስብርባሪዎች ምክንያት ተጠራ።
3እንዲህ በል፦ የይሁዳ ነገሥታት፣ የኢየሩሳሌምም ነዋሪዎች ሆይ፤ የአባታችንን ቃል ስሙ። የሰማይ ሠራዊት አባት፣ የእስራኤል አባት፣ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፣ የሚሰማ ሁሉ ጆሮ እስኪቃጨል ድረስ በዚህ ስፍራ ላይ መቅሠፍት አመጣለሁ። 4እኔን ስለ ተዉኝ ይህንም ስፍራ ባዕድ ስላደረጉ፣ እነርሱ፣ አባቶቻቸውና የይሁዳ ነገሥታት ለማያውቋቸው ሌሎች አማልክት በዚህ ዕጣን ስላጠኑ፣ ይህንም ስፍራ በንጹሕ ደም ስለ ሞሉት ነው። 5ወንዶች ልጆቻቸውን ለበኣል የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገው በእሳት ለማቃጠል የበኣልን የኰረብታ መስገጃዎች ሠሩ፤ ይህም ያላዘዝሁት፣ ያልተናገርሁትና በልቤ ያልታሰበ ነገር ነው። 6ስለዚህ እነሆ፣ ይህ ስፍራ ከእንግዲህ ቶፌት ወይም የቤንሂኖም ሸለቆ ሳይሆን የእልቂት ሸለቆ ተብሎ የሚጠራበት ቀን ይመጣል፤ ይላል አባታችን። 7በዚህ ስፍራ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ዕቅድ አፈሳለሁ፤ በጠላቶቻቸው ፊት፣ ነፍሳቸውን በሚሹ እጅ በሰይፍ እንዲወድቁ አደርጋለሁ፤ በድናቸውንም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት ምግብ አድርጌ እሰጣለሁ። b b v7 እዚህ ላይ “አፈሳለሁ” የሚለው ቃል ኤርምያስ ይዞት የነበረውን የሸክላ ማሰሮ ከሚያመለክተው ቃል ጋር ይመሳሰላል፤ ባዶ የሆነው ማሰሮ የይሁዳን ባዶ የሆነ ዕቅድ ያመለክታል። 8ይህችን ከተማ አስፈሪ፣ የመሳለቂያም አደርጋታለሁ፤ በአጠገቧ የሚያልፍ ሁሉ ይደነግጣል፣ በቍስሏም ሁሉ ይሳለቃል። 9የወንዶችና የሴቶች ልጆቻቸውን ሥጋ አበላቸዋለሁ፤ ጠላቶቻቸውና ነፍሳቸውን የሚሹ በከበቡትና ባስጨነቋቸው ጊዜ እያንዳንዱ የባልንጀራውን ሥጋ ይበላል።
10ከዚያም ከአንተ ጋራ በሄዱት ሰዎች ፊት ማሰሮውን ስበር፣
11እንዲህም በላቸው፦ የሰማይ ሠራዊት አባት እንዲህ ይላል፦ አንድ ሰው ዳግመኛ ሊጠገን በማይችል ሁኔታ የሸክላ ሠሪን ዕቃ እንደሚሰብር፣ እንዲሁ ይህን ሕዝብና ይህችን ከተማ እሰብራለሁ፤ ለመቅበርም ሌላ ስፍራ ስለሌለ በቶፌት ይቀብራሉ። 12በዚህ ስፍራና በነዋሪዎቹ ላይ የማደርገው ይህ ነው፤ ይላል አባታችን፤ ይህችንም ከተማ እንደ ቶፌት አደርጋለሁ። 13የኢየሩሳሌም ቤቶችና የይሁዳ ነገሥታት ቤቶች እንደ ቶፌት ርኩስ ይሆናሉ፤ በጣራቸው ላይ ለሰማይ ሠራዊት ሁሉ ዕጣን ያጠኑባቸው፣ ለሌሎችም አማልክት የመጠጥ ቍርባን ያፈሰሱባቸው ቤቶች ሁሉ ናቸው።
14አባታችን ትንቢት እንዲናገር ከላከው ከቶፌት ኤርምያስ መጥቶ፣ በአባታችን ቤት አደባባይ ቆሞ ለሕዝቡ ሁሉ እንዲህ አለ፦
15የሰማይ ሠራዊት አባት፣ የእስራኤል አባታችን እንዲህ ይላል፦ ዐንገታቸውን አደንድነው ቃሌን ለመስማት እምቢ ብለዋልና በዚህች ከተማና በመንደሮቿ ሁሉ ላይ በእርሷ ላይ የተናገርሁትን መቅሠፍት ሁሉ አመጣለሁ።