ቅን ነገር የሚያደርግ የለም
ለመዘምራን አለቃ፤ እንደ መሃላት ዜማ የተዘመረ፤ የዳዊት የጥበብ መዝሙር።
ከመዝሙር 14 ጋር ተመሳሳይ ነው ማለት ይቻላል። አብ የሚያስተውል አንድ ሰው ፍለጋ የሰውን ልጆች ሁሉ ይመለከታል፤ አንድም አያገኝም። ሕዝቡን የሚበሉ፣ የሚያስፈራ ነገር በሌለበት ፍርሃት ይይዛቸዋል። ከጽዮን የሚመጣውን ማዳን በመናፈቅ ይደመደማል።
53 1ተላላው በልቡ፣ “እግዚአብሔር የለም” ይላል። ጠማሞች ናቸው፤ አስጸያፊ በደልን ያደርጋሉ፤ ቅን ነገር የሚያደርግ የለም።
2አስተዋይ ያለ፣ አባታችንን የሚሻ ይኖር እንደ ሆነ ያይ ዘንድ፣ አባታችን ከሰማይ በሰው ልጆች ሁሉ ላይ ተመለከተ። 3ሁሉ ተስተዋል፤ በአንድነት ጠማማ ሆነዋል፤ ቅን ነገር የሚያደርግ የለም፤ አንድ ስንኳ የለም።
4እንጀራ እንደሚበሉ ሕዝቤን የሚበሉ፣ አባታችንንም የማይጠሩ፣ የክፋት አድራጊዎች እውቀት የላቸውምን? 5የሚያስፈራ ነገር በሌለበት፣ በዚያ በታላቅ ፍርሃት ተውጠው ነበር፤ አባታችን በአንተ ላይ ያደፈጠውን ሰው ዐጥንት በትኖአልና፤ አባታችን ጠልቶአቸዋልና አሳፈርሃቸው።
6ለእስራኤል የሚሆን ድነት ከጽዮን ምነው በወጣ! አባታችን የሕዝቡን ምርኮ በመለሰ ጊዜ፣ ያዕቆብ ደስ ይበለው፣ እስራኤል ሐሴት ያድርግ።