የአባታችን ሰይፍ በፍልስጥኤም ላይ ይወርዳል
የአብ ጐርፍ ከሰሜን ተነሥቶ ፍልስጥኤምን አጥለቀለቀ፤ ድንገተኛነቱ ታላቅ ስለሆነ አባቶች ወደ ልጆቻቸው ዘወር አይሉም። ጋዛና አስቀሎና ያለቅሳሉ። በመጨረሻም ሰይፉ እስከ መቼ ድረስ አታርፍም ተብሎ ይጠየቃል፤ መልሱም፦ ገና ትእዛዝ እያለበት አያርፍም የሚል ነው።
47 1ፈርዖን ጋዛን ከመምታቱ በፊት፣ ስለ ፍልስጥኤማውያን ወደ ነቢዩ ኤርምያስ የመጣው የአባታችን ቃል ይህ ነው።
2አባታችን እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፣ ውሃ ከሰሜን ይጎርፋል፣ ተጥለቅላቂ ጎርፍም ይሆናል። ምድሪቱንና በውስጧ ያለውን ሁሉ፣ ከተማዪቱንና ነዋሪዎቿን ያጥለቀልቃል። ሕዝቡም ይጮኻል፣ በምድሪቱ የሚኖርም ሁሉ ዋይ ዋይ ይላል። 3በፈረሶቹ ኮቴ ድምፅ፣ በሠረገላዎቹ ጩኸትና በመንኰራኵሮቹ ግሥጋሤ፣ አባቶች እጆቻቸው ዝለው ስለ ልጆቻቸው ወደ ኋላ አይመለሱም፣ 4ፍልስጥኤማውያንን ሁሉ ለማጥፋት የሚመጣው ቀን ስለ ደረሰ፣ ሊረዳ የሚችለውን የተረፈውን ሁሉ ከጢሮስና ከሲዶና ለመቍረጥ ነው። አባታችን ፍልስጥኤማውያንን፣ ከከፍቶር ባሕር ዳርቻ የቀሩትን ያጠፋልና። 5ጋዛ በሐዘን ራሷን ትላጫለች፤ አስቀሎና ዝም ትሰኛለች። እናንተ የሸለቆአቸው ቀሪዎች ሆይ፣ እስከ መቼ ድረስ ሰውነታችሁን ትተለትላላችሁ? 6ወዮ፣ የአባታችን ሰይፍ ሆይ! እስከ መቼ ድረስ አታርፍም? ወደ ሰገባህ ተመለስ፤ ጸጥ በልና ዕረፍ። 7አባታችን ትእዛዝ ከሰጠው ታዲያ እንዴት ሊያርፍ ይችላል? በአስቀሎና ላይና በባሕሩ ዳርቻ ላይ፣ ወደዚያ መርቶታል።”