አባታችን ተናገረ
አብ ዐሥሩን ቃላት ራሱ ይናገራል፤ የሚጀምረውም በትእዛዝ ሳይሆን ማን እንደ ሆነ በመግለጥ ነው፦ ከባርነት ያወጣቸው እርሱ። ታማኝነት፣ ስም፣ ሰንበት፣ ወላጆች፣ ሕይወት፣ ጋብቻ፣ ንብረት፣ እውነት፣ ምኞት። ሕዝቡ ሙሴ ስለ እነርሱ እንዲሰማ ይለምናሉ፤ እርሱም ወደ ድቅድቁ ጨለማ ይገባል።
20 1ከዚያም አባታችን ይህን ሁሉ ቃል ተናገረ፦
2“ከግብፅ ምድር፣ ከባርነት ቤት ያወጣሁህ አባትህ እኔ ነኝ።
3“ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይኑሩህ።
4“በላይ በሰማይ፣ በታች በምድር፣ ወይም ከምድር በታች በውሃ ውስጥ ያለውን የማናቸውንም ነገር ምስል የተቀረጸ ጣዖት ለራስህ አታድርግ። 5ለእነርሱ አትስገድ፤ አታምልካቸውም፤ እኔ አባትህ ቀናተኛ አባት ነኝና፤ የሚጠሉኝን የአባቶችን ኀጢአት እስከ ሦስተኛውና እስከ አራተኛው ትውልድ ድረስ በልጆቻቸው ላይ አመጣለሁ፤ 6ለሚወድዱኝና ትእዛዛቴን ለሚጠብቁ ግን እስከ ሺሕ ትውልድ ድረስ የኪዳን ፍቅር አሳያለሁ።
7“የአባትህን ስም በከንቱ አትጥራ፤ አባታችን ስሙን በከንቱ የሚጠራውን ከበደል ነጻ አያደርገውምና።
8“የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ። 9ስድስት ቀን ትደክማለህ፤ ሥራህንም ሁሉ ትሠራለህ፤ 10ሰባተኛው ቀን ግን ለአባትህ ሰንበት ነው። በእርሱ ምንም ሥራ አትሥራ፤ አንተም፣ ወንድ ልጅህም፣ ሴት ልጅህም፣ ወንድ ባሪያህም፣ ሴት ባሪያህም፣ ከብትህም፣ በደጆችህም ውስጥ ያለ መጻተኛም። 11አባታችን በስድስት ቀን ሰማይን፣ ምድርን፣ ባሕርን፣ በእነርሱም ውስጥ ያለውን ሁሉ ሠርቶ በሰባተኛው ቀን ዐረፈና፤ ስለዚህ አባታችን የሰንበትን ቀን ባረከ፤ ቀደሰውም።
12“አባትህን ና እናትህን አክብር፤ አባትህ በሚሰጥህ ምድር ዕድሜህ ይረዝም ዘንድ።
13“አትግደል።
14“አታመንዝር።
15“አትስረቅ።
16“በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር።
17“የባልንጀራህን ቤት አትመኝ። የባልንጀራህን ሚስት፣ ወንድ ባሪያውን ወይም ሴት ባሪያውን፣ በሬውን ወይም አህያውን፣ ወይም የባልንጀራህ የሆነውን ማናቸውንም ነገር አትመኝ።”
18ሕዝቡም ሁሉ ነጎድጓዱን፣ የመብረቁን ብልጭታ፣ የመለከቱን ድምፅ፣ ተራራውንም ሲጢስ አዩ። ይህን ባዩ ጊዜ ተንቀጠቀጡ፤ በሩቅም ቆሙ።
19ሙሴንም፣ “አንተ ተናገረን፤ እኛም እንሰማለን። አባታችን ግን አይናገረን፤ አለዚያ እንሞታለን” አሉት።
20ሙሴም ሕዝቡን፣ “አትፍሩ፤ አባታችን ሊፈትናችሁ መጥቷል፤ ፍርሃቱም ከእናንተ ጋራ ይኖር ዘንድ፣ እናንተም ኀጢአት እንዳትሠሩ ነው” አላቸው። 21ሕዝቡ ርቀው ቆሙ፤ ሙሴ ግን አባታችን ወደ ነበረበት ጭጋጋማ ጨለማ ቀረበ።
ሙሴ ቀረበ
22ከዚያም አባታችን ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ለእስራኤላውያን እንዲህ ንገራቸው፦ ከሰማይ ሆኜ ከእናንተ ጋራ እንደ ተናገርኋችሁ ራሳችሁ አይታችኋል። 23ከእኔ ጋራ የሚቆሙ የብር አማልክት አታድርጉ፤ የወርቅ አማልክትም ለራሳችሁ አትሥሩ። 24ከመሬት መሠዊያ ሥራልኝ፤ በእርሱም ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕትህን ና የደኅንነትህን መሥዋዕት፣ መንጎችህንና ከብቶችህን አቅርብ። ስሜ የሚታሰብበት ስፍራ ሁሉ ወደ አንተ እመጣለሁ፤ እባርክህማለሁ። 25የድንጋይ መሠዊያ ብትሠራልኝ፣ በተጠረቡ ድንጋዮች አትሥራው፤ በእርሱ ላይ መሣሪያህን ማንሣትህ ያረክሰዋልና። 26ኀፍረተ ሰውነትህ በእርሱ ላይ እንዳይገለጥ፣ ወደ መሠዊያዬ በመሰላል አትውጣ።”