ያንብቡ። ይቀበሉ። ይጠቁሙ።

♥ አስተያየቶች

አስቴር 7

መጽሐፍ

አስቴር ስለ ሕዝቧ ተማጸነች

በሁለተኛው ግብዣ አስቴር በመጨረሻ ለራሷና ለሕዝቧ ሕይወት ትለምናለች፤ የሸጣቸውንም ሰው በስም ትጠራለች፦ ሐማ። ንጉሡ በቁጣ ተነሥቶ ይወጣል፤ ሐማ እየለመነ በአልጋዋ ላይ ይወድቃል፤ ይህም እንደ ጥቃት ይቆጠራል። በገዛ ግንዱ ላይ ይሰቀላል።

ምዕራፍ 7።

ንጉሡና ሃማም ከንግሥት አስቴር ጋራ ሊጠጡ መጡ። በሁለተኛውም ቀን ንጉሡ የወይን ጠጅ ሲጠጡ እንደ ገና፣ “ንግሥት አስቴር ሆይ፤ ልመናሽ ምንድን ነው? ይፈጸምልሻል። ጥያቄሽስ? እስከ መንግሥቴ እኵሌታ ድረስ ቢሆን እንኳ ይደረግልሻል” ሲል ጠየቀ።

ንግሥት አስቴርም መልሳ እንዲህ አለች፤ “ንጉሥ ሆይ፤ በፊትህ ሞገስ አግኝቼ እንደ ሆነ፣ ንጉሡንም ደስ የሚያሰኘው ከሆነ፣ በልመናዬ ሕይወቴ፣ በጥያቄዬም ሕዝቤ ይሰጠኝ። እኔና ሕዝቤ እንድንጠፋ፣ እንድንገደል፣ እንድንደመሰስ ተሽጠናልና። ለወንድና ለሴት ባሪያነት ብቻ ተሽጠን ቢሆን ኖሮ ዝም ባልኩ ነበር፤ እንዲህ ያለው መከራ ንጉሡን ለማስቸገር የሚያበቃ አይደለምና።”

ንጉሥ አርጤክስስም ንግሥት አስቴርን፣ “ይህን ለማድረግ የሚደፍር ማን ነው? የትስ አለ?” አላት።

አስቴርም፣ “ባላጋራውና ጠላቱ ይህ ክፉ ሃማ ነው!” አለች። ሃማም በንጉሡና በንግሥቲቱ ፊት ደነገጠ።

ንጉሡም በቍጣ ተነሥቶ ከወይን ጠጁ ወደ ቤተ መንግሥቱ አትክልት ስፍራ ወጣ፤ ሃማ ግን ንጉሡ ጥፋቱን እንደ ቈረጠበት ስላየ ስለ ሕይወቱ ንግሥት አስቴርን ለመለመን ቀረ። ንጉሡም ከቤተ መንግሥቱ አትክልት ስፍራ ወደ ግብዣው አዳራሽ ተመለሰ። ሃማም አስቴር ባለችበት አልጋ ላይ ወድቆ ነበር። ንጉሡም፣ “እኔ በዚሁ ሳለሁ ንግሥቲቱን እስከ መድፈር ይደርሳል?” አለ። ይህም ቃል ከአፉ ሳይወጣ አገልጋዮቹ የሃማን ፊት ሸፈኑ። a a v8 የተፈረደበትን ሰው ፊት መሸፈን ዕጣ ፈንታው እንደ ተወሰነ የሚያመለክት የጥንት ምልክት ነበር፤ እርሱም እንደ ሞተ ይቈጠር ነበር።

ከንጉሡ ጃንደረቦች አንዱ ሐርቦና፣ “ሃማ ለንጉሡ መልካም ለተናገረው ለመርዶክዮስ ያሠራው ሰባ አምስት ጫማ የሚረዝም መስቀያ በሃማ ቤት ቆሞአል” አለ። ንጉሡም፣ “በእርሱ ላይ ስቀሉት” አለ።

ስለዚህ ለመርዶክዮስ ባዘጋጀው መስቀያ ላይ ሃማን ሰቀሉት፤ የንጉሡም ቍጣ በረደ።

A young man reading the Father's Heart Bible (FHB) print edition in a coffee shop አሁን በኅትመት ይገኛል

አስተያየቶች

ሐሳብ፣ ጥያቄ፣ ወይም ይህ ምዕራፍ በልብዎ ያነሣሣው ቃል — እዚህ ያካፍሉ። እያንዳንዱ አስተያየት ስምዎን በአስተዋጽኦ አበርካቾች ግድግዳ ላይ ያሰፍራል።

ማንበብ፣ ማዳመጥ፣ መቅዳትና ማጋራት ለሁሉም ክፍት ነው — መለያ አያስፈልግም። አስተያየት መስጠት፣ ቁጥሮችን ማድመቅና የደረሱበትን ቦታ ምልክት ማድረግ ከነጻ መለያ ጋራ ይመጣሉ፤ እያንዳንዱ አስተያየትም ስምዎን በአስተዋጽኦ አበርካቾች ግድግዳ ላይ ያሰፍራል።

ቤተሰቡን ይቀላቀሉ — በነጻ ነው →
  • እስካሁን ምንም አስተያየት የለም። ድምፅዎን በማሰማት የመጀመሪያው ይሁኑ።