የተረፉት ወደ ግብፅ ሸሹ
ዮሐናንና ሌሎቹ ኤርምያስን ሐሰተኛ ብለው አብ እንዳልላከው ካዱ፤ ባሮክንም ወቀሱ፤ ከዚያም ቅሬታውን ሁሉ ኤርምያስንም ጭምር ይዘው ወደ ግብፅ ሄዱ። በጣፍናስ የናቡከደነፆር ዙፋን በሚቆምበት ስፍራ ድንጋዮችን ቀበረ። የሸሹት አደጋ እየተከተላቸው ነው።
43 1ኤርምያስ ለሕዝቡ ሁሉ የአባታቸውን ቃል ሁሉ፣ አባታቸው እንዲነግራቸው የላከውን ቃል ሁሉ ነግሮ በጨረሰ ጊዜ፣ 2የሆሻያ ልጅ አዛርያ፣ የቃሬህ ልጅ ዮሐናን፣ ትዕቢተኞቹም ሰዎች ሁሉ ኤርምያስን እንዲህ አሉት፤ “ሐሰት እየተናገርህ ነው! አባታችን፣ ‘ወደ ግብፅ ሄዳችሁ አትቀመጡ’ ብለህ እንድትናገር አልላከህም። 3ነገር ግን የኔርያ ልጅ ባሮክ፣ ይገድሉን ዘንድ ወይም ወደ ባቢሎን ይማርኩን ዘንድ ለባቢሎናውያን አሳልፎ ሊሰጠን በእኛ ላይ ያነሣሣሃል።”
4ስለዚህ የቃሬህ ልጅ ዮሐናን፣ የጦር አዛዦቹ ሁሉ፣ ሕዝቡም ሁሉ በይሁዳ ምድር ይኖሩ ዘንድ የተነገረውን የአባታችንን ድምፅ አልታዘዙም። 5ስለዚህ የቃሬህ ልጅ ዮሐናንና የጦር አዛዦቹ ሁሉ፣ ተበትነውበት ከነበሩት አሕዛብ ሁሉ በይሁዳ ምድር ለመኖር ተመልሰው የመጡትን የይሁዳን ቅሬታ ሁሉ ወሰዱ፤ 6ወንዶቹን፣ ሴቶቹን፣ ልጆቹን፣ የንጉሡን ሴቶች ልጆች፣ የዘበኞች አለቃ ነቡዛራዳን ከሻፋን ልጅ ከአኪቃም ልጅ ከጎዶልያ ጋር ትቶት የነበረውን ሁሉ፣ ነቢዩ ኤርምያስንና የኔርያን ልጅ ባሮክን ወሰዱ። 7ስለዚህ የአባታችንን ድምፅ ባለመታዘዝ ወደ ግብፅ ገቡ፤ እስከ ጣፍናስም መጡ።
8የአባታችንም ቃል በጣፍናስ ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፤
9“የይሁዳ ሰዎች እያዩህ፣ ትልልቅ ድንጋዮች በእጅህ ይዘህ በጣፍናስ ባለው በፈርዖን ቤተ መንግሥት መግቢያ ላይ ባለው በጡብ ንጣፍ፣ በሸክላ ጭቃ ውስጥ ቅበራቸው። 10ከዚያም እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ ‘የሰማይ ሠራዊት አባት፣ የእስራኤል አባታችን እንዲህ ይላል፤ እነሆ፣ ባሪያዬን የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን እልካለሁ፤ እዚህ በቀበርኋቸው በእነዚህ ድንጋዮች ላይ ዙፋኑን አኖራለሁ፤ በላያቸውም ንጉሣዊ ድንኳኑን ይዘረጋል። 11መጥቶም ግብፅን ይመታል፤ ለሞት ለተወሰኑት ሞት፣ ለምርኮ ለተወሰኑት ምርኮ፣ ለሰይፍ ለተወሰኑት ሰይፍ ይሆናል። 12በግብፅ አማልክት ቤተ መቅደሶች እሳት አነድዳለሁ፤ ናቡከደነፆርም ያቃጥላቸዋል፣ ይማርካቸዋልም። እረኛ ልብሱን እንደሚከናነብ የግብፅን ምድር በራሱ ላይ ይከናነባል፤ ያለ ጉዳትም ከዚያ ይወጣል። 13በግብፅ ምድር ያሉትን የሄልዮቡሊስን የተቀደሱ ዐምዶች ይሰብራል፤ የግብፅንም አማልክት ቤተ መቅደሶች በእሳት ያቃጥላል።’” a a v13 እዚህ “ቤትሳሚስ” (“የፀሐይ ቤት”) ማለት ግሪኮች ሄልዮቡሊስ ብለው የጠሩት የግብፅ ከተማ ሲሆን፣ የግብፅ የፀሐይ አምልኮ ማዕከል ነው፤ በይሁዳ የሚገኘው ተመሳሳይ ስም ያለው ከተማ አይደለም።