የአባታችን የምሕረት ምልክት
አብ የጦር መሣሪያ የያዙ ስድስት ሰዎችን ጠራ፤ በፍታ የለበሰና የጸሓፊ ቀለም ቀንድ የያዘው አንዱ ሰው በከተማይቱ ክፋት የሚያዝኑትን ሁሉ በግንባራቸው ላይ ምልክት አደረገ። የቀሩት ከመቅደሱ ጀምሮ ተመቱ። ሕዝቅኤል በግንባሩ ተደፍቶ የሚተርፍ ሰው ይኖር እንደሆነ ጠየቀ።
9 1ከዚያም በታላቅ ድምፅ በጆሮዬ እንዲህ ሲል ጮኸ፤ “የከተማዪቱ ጠባቂዎች ሆይ፣ እያንዳንዳችሁ የጥፋት መሣሪያችሁን በእጃችሁ ይዛችሁ ቅረቡ።”
2ስድስት ሰዎች ወደ ሰሜን ትይዩ ካለው ከላይኛው በር መጡ፤ እያንዳንዳቸውም ገዳይ መሣሪያ በእጃቸው ያዙ፤ በመካከላቸውም የተልባ እግር ልብስ የለበሰ፣ በወገቡም የመጻፊያ መሣሪያ ያለው ሰው ነበረ። መጥተውም በናስ መሠዊያው አጠገብ ቆሙ።
3የአባታችንም ክብር ዐርፎበት ከነበረው ከኪሩቤሉ በላይ ተነሥቶ ወደ ቤቱ ደጃፍ መጣ። የተልባ እግር ልብስ የለበሰውንና በወገቡ የመጻፊያ መሣሪያ ያለውን ሰው ጠራው።
4አባታችንም እንዲህ አለው፤ “በኢየሩሳሌም ከተማ ውስጥ ዐልፈህ፣ በዚያ በሚፈጸመው አስጸያፊ ነገር ሁሉ ላይ የሚያለቅሱትንና የሚያቃስቱትን ሰዎች ግንባር ምልክት አድርግባቸው።” a a v4 ለደኅንነት ምልክት የተደረገባቸው በዙሪያቸው ባለው ኀጢአት ልባቸው የሚሰበር ናቸው፤ አባታችን እርሱን በሚያሳዝነው ነገር የሚያዝኑትን ልጆች ይምራል፣ በማኅተሙም ያትማል።
5ለሌሎቹም በጆሮዬ እንዲህ አለ፤ “ተከትላችሁት በከተማዪቱ ውስጥ ዐልፋችሁ ምቱ። ዐይናችሁ አይራራ፣ አትዘኑም። 6ሽማግሌዎችን፣ ጐበዛዝትን፣ ቈነጃጅትን፣ ሕፃናትንና ሴቶችን ሁሉ ግደሉ፤ ነገር ግን ምልክት ያለበትን ማንንም አትንኩ። ከመቅደሴም ጀምሩ።” እነርሱም በቤቱ ፊት ለፊት ካሉት ሽማግሌዎች ጀመሩ።
7ከዚያም፣ “ቤቱን አርክሱ፣ አደባባዮቹንም በሙታን ሙሉ። ውጡ!” አላቸው። እነርሱም ወጥተው በከተማዪቱ ውስጥ ያሉትን ሰዎች መቱ።
8እነርሱም ሲመቱ እኔ ብቻዬን ቀረሁ፤ በፊቴም ተደፍቼ፣ “ወዮ፣ ጌታ አባት ሆይ! በኢየሩሳሌም ላይ መዓትህን በምታፈስበት ጊዜ የእስራኤልን ቅሬታ ሁሉ ታጠፋለህን?” ብዬ ጮኽሁ።
9እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “የእስራኤልና የይሁዳ ቤት በደል እጅግ ታላቅ ነው። ምድሪቱ በደም ማፍሰስ ተሞልታለች፣ ከተማዪቱም በግፍ ተሞልታለች፤ ‘እግዚአብሔር ምድሪቱን ተወ፣ እግዚአብሔርም አያይም’ ይላሉና። 10እኔም አልራራላቸውም፣ አልምራቸውምም። ሥራቸውን በራሳቸው ራስ ላይ አመጣለሁ።”
11ከዚያም የተልባ እግር ልብስ የለበሰውና በወገቡ የመጻፊያ መሣሪያ ያለው ሰው፣ “ያዘዝኸኝን አድርጌአለሁ” ብሎ መለሰ።