አባታችን የሚሠራበት ቀን
አብ አባታችን በሚሠራባት በአንዲት ቀን ሁለት ዕጣ ፈንታዎች፦ ትዕቢተኞች እንደ ገለባ ይቃጠላሉ፤ ስሙን የሚፈሩ ግን ከጋጥ እንደ ተፈቱ ጥጆች እየዘለሉ ይወጣሉ። ኤልያስ አስቀድሞ እንደሚመጣ ተስፋ ተሰጥቷል — የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች፣ የልጆችንም ልብ ወደ አባቶች እንዲመልስ ይላካል።
4 1እነሆ፣ እንደ እቶን የሚነድ ቀን ይመጣል፤ በዚያ ቀን ትዕቢተኞች ሁሉና ክፉ አድራጊ ሁሉ ገለባ ይሆናሉ፤ ያም ቀን ሥርም ቅርንጫፍም ሳያስቀርላቸው ያቃጥላቸዋል ይላል የሰማይ ሠራዊት አባት። 2ነገር ግን ስሜን ለምትፈሩ ለእናንተ የጽድቅ ፀሐይ በክንፎቿ ፈውስን ይዛ ትወጣለች፤ እናንተም ከጋጣ እንደሚወጡ ጥጆች እየዘለላችሁ ትወጣላችሁ። 3ክፉዎችንም ትረግጣላችሁ፤ በምሠራበት ቀን በእግራችሁ ጫማ ሥር አመድ ይሆናሉና ይላል የሰማይ ሠራዊት አባት።
4“የባሪያዬን የሙሴን ሕግ፣ ለእስራኤል ሁሉ በኮሬብ ያዘዝሁትን ሥርዓትና ፍርድ አስታውሱ።
5እነሆ፣ ታላቁና የሚያስፈራው የአባታችን ቀን ሳይመጣ ነቢዩን ኤልያስን እልክላችኋለሁ። a a v5 ኢየሱስ መጥምቁን ዮሐንስን እዚህ ላይ ተስፋ የተሰጠው ኤልያስ እንደ ሆነ፣ ልባቸውን ለእርሱ ሊያዘጋጅ የመጣው እርሱ እንደ ሆነ ገለጸ (ማቴዎስ 11፥14፤ 17፥10-13)። 6የአባቶችን ልብ ወደ ልጆቻቸው፣ የልጆችንም ልብ ወደ አባቶቻቸው ይመልሳል፤ ይህም መጥቼ ምድርን በፍጹም ጥፋት እንዳልመታ ነው።”