አሽዶድ በአሦር እጅ ወደቀች
አብ ኢሳይያስን ማቅና ጫማውን አውልቆ ለሦስት ዓመት ራቁቱንና ባዶ እግሩን እንዲሄድ ይነግረዋል — ተጋልጠው የሚነዱ ምርኮኞች ሕያው ምስል። ይህም በእነዚያ አጋሮች ላይ ባለው የይሁዳ መታመን ላይ ያነጣጠረ ነው። የባሕሩ ዳርቻ እንዴት እናመልጣለን ብሎ ይጠይቃል።
20 1በአሦር ንጉሥ በሳርጎን ተልኮ የጦር አዛዡ ወደ አሽዶድ በመጣበት ዓመት፣ አሽዶድን ወግቶ ያዛት።
2በዚያን ጊዜ አባታችን በአሞጽ ልጅ በኢሳይያስ አማካይነት፣ “ማቅህን ከወገብህ ፍታ፤ ጫማህንም ከእግርህ አውልቅ” አለ። እርሱም እንዲሁ አደረገ፤ ዕራቁቱንና ባዶ እግሩን እየሄደ ኖረ። 3ከዚያም አባታችን እንዲህ አለ፤ “ባሪያዬ ኢሳይያስ በግብፅና በኵሽ ላይ ምልክትና ትእምርት እንዲሆን፣ ዕራቁቱንና ባዶ እግሩን ሦስት ዓመት እንደ ሄደ ሁሉ፣ a a v3 ኵሽ አሁን ሱዳንንና የሰሜን ኢትዮጵያን የሚሸፍነው አካባቢ ጥንታዊ ስም ነው። 4እንዲሁ የአሦር ንጉሥ የግብፅን ምርኮኞችና የኵሽን ግዞተኞች፣ ወጣቱንም ሽማግሌውንም ዕራቁታቸውን፣ ባዶ እግራቸውን፣ መቀመጫቸው ተገልጦ ይነዳቸዋል፤ ይኸውም የግብፅን ኀፍረት ያጋልጣል። 5ከዚያም ተስፋቸው በሆነችው በኵሽና ትምክሕታቸው በሆነችው በግብፅ ምክንያት ይደነግጣሉ፤ ያፍራሉም። 6በዚያም ቀን የዚህ ባሕር ዳርቻ ሕዝብ እንዲህ ይላሉ፤ ‘እነሆ፣ ከአሦር ንጉሥ እንድንድን ለርዳታ የሸሸንበት ተስፋችን እንዲህ ሆነ! እኛስ እንዴት እናመልጣለን?’”