ኢዮአስ አባታችን ተስፋ የሰጠው ንጉሥ ሆኖ ነገሠ
ዮዳሄ ዘበኞቹን ያደራጃል፣ የተሸሸገውን ልጅ ያወጣል፣ ዘውድ ይጭንለታል፣ ንጉሡ ሺህ ዓመት ይንገሥ ብሎም ይጮኻል። ጎቶልያ ልትገደል ከቤተ መቅደሱ ውጭ ትወሰዳለች፣ የበኣል ቤት ይፈርሳል፣ ካህኑ፣ ሕዝቡና ንጉሡም የአብ ሕዝብ ለመሆን በአንድነት ቃል ኪዳን ያደርጋሉ።
23 1በሰባተኛው ዓመት ዮዳሄ ተበረታ፤ ከመቶ አለቆች ጋራ ኪዳን ገባ፤ እነርሱም የኢያሮሐም ልጅ አዛርያ፣ የዮሐናን ልጅ እስማኤል፣ የዖቤድ ልጅ አዛርያ፣ የዓዳያ ልጅ መዓሥያና የዝክሪ ልጅ ኤሊሳፍጥ ነበሩ። 2በይሁዳ ዙሪያ ተዘዋውረው ሌዋውያንን ከከተሞችዋ ሁሉ የእስራኤልንም የቤተ ሰብ አለቆች ሰብስበው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ። 3ጉባኤው ሁሉ በአባታችን ቤት ከንጉሡ ጋራ ኪዳን ገባ። ዮዳሄም እንዲህ አላቸው፤ “እነሆ፣ አባታችን ስለ ዳዊት ልጆች ተስፋ እንደ ሰጠው የንጉሡ ልጅ ይነግሣል። 4የምታደርጉት ይህ ነው፤ ከእናንተ ሲሶው፣ ማለትም በሰንበት የሚገቡት ካህናትና ሌዋውያን፣ በመግቢያዎች ደጃፍ ላይ በር ጠባቂዎች ይሁኑ። 5ሲሶው በንጉሡ ቤት፣ ሲሶው በመሠረት በር፣ ሕዝቡም ሁሉ በአባታችን ቤት አደባባዮች ይሁኑ። 6ከካህናትና ከሚያገለግሉት ሌዋውያን በቀር ማንም ወደ አባታችን ቤት አይግባ፤ እነርሱ የተቀደሱ ስለ ሆኑ ይግቡ። የቀረው ሁሉ ለአባታችን ይጠብቅ። 7ሌዋውያን እያንዳንዳቸው የጦር መሣሪያቸውን በእጃቸው ይዘው ንጉሡን ይከብቡ፤ ወደ ቤቱ የሚገባ ሁሉ ይገደል። በሚገባበትና በሚወጣበት ሁሉ ከንጉሡ ጋራ ሁኑ።”
8ሌዋውያንና ይሁዳ ሁሉ ካህኑ ዮዳሄ ያዘዛቸውን በትክክል አደረጉ። ካህኑ ዮዳሄ ከክፍሎቹ አንዱንም ስላላሰናበተ፣ እያንዳንዱ በሰንበት ወደ ተረኝነት የሚገቡትን ከሚወጡት ጋራ ይዞ መጣ። 9ካህኑ ዮዳሄም በአባታችን ቤት የተቀመጡትን የንጉሥ ዳዊትን ጦሮችና ትልልቅና ትናንሽ ጋሻዎች ለመቶ አለቆች ሰጠ። 10ሕዝቡንም ሁሉ እያንዳንዱ የጦር መሣሪያውን በእጁ ይዞ፣ ከቤተ መቅደሱ ደቡብ ወገን እስከ ሰሜን ወገን፣ መሠዊያውን፣ ቤተ መቅደሱንና ንጉሡን ከብበው እንዲቆሙ አደረገ። 11የንጉሡንም ልጅ አወጡት፤ ዘውድ ደፉለት፤ የኪዳኑን ሕግ ሰጡት፤ አነገሡትም። ዮዳሄና ልጆቹም ቀብተውት፣ “ንጉሡ ለዘላለም ይኑር!” ብለው ጮኹ። a a v11 ምስክሩ የአባታችን የኪዳን ሕግ ቅጅ ነበር፤ አዲሱ ንጉሥ በራሱ ሥልጣን ሳይሆን በአባታችን ሥልጣን ሥር እንደሚገዛ ምልክት እንዲሆን በእጆቹ ተሰጠው።
የአባታችን ቤት ዙፋኑን የነጠቀችውን ንግሥት አስወጣ
12ዓታልያም ሕዝቡ ሲሮጥና ንጉሡን ሲያወድስ ድምፁን ሰምታ፣ በአባታችን ቤት ወደ እነርሱ መጣች። 13ተመለከተችም፤ እነሆ ንጉሡ በመግቢያው አጠገብ ባለው ዓምዱ ላይ ቆሞ ነበር፤ አለቆችና መለከት ነፊዎች በአጠገቡ ነበሩ፤ የአገሩም ሕዝብ ሁሉ ደስ እያለው መለከት ይነፋ ነበር፤ ዘማሪዎችም በመሣሪያ ምስጋናውን ይመሩ ነበር። ያን ጊዜ ዓታልያ ልብሷን ቀደደችና፣ “ክህደት! ክህደት!” ብላ ጮኸች።
14ካህኑ ዮዳሄም በሰራዊቱ ላይ የተሾሙትን የመቶ አለቆች ጠርቶ፣ “በተሰለፉት መካከል አሳልፋችሁ አውጧት፤ የሚከተላትንም ሁሉ በሰይፍ ግደሉ” አላቸው። ካህኑ፣ “በአባታችን ቤት አትግደሏት” ብሎ ነበርና። 15ያዟትም፤ በንጉሡ ቤት አጠገብ ወዳለው የፈረስ በር መግቢያ በደረሰች ጊዜ፣ በዚያ ገደሏት።
ዮዳሄ የአባታችንን ኪዳንና ቤት አደሰ
16ከዚያም ዮዳሄ የአባታችን ሕዝብ እንዲሆኑ በራሱና በሕዝቡ ሁሉ በንጉሡም መካከል ኪዳን አደረገ። 17ሕዝቡም ሁሉ ወደ በኣል ቤት ሄደው አፈረሱት፤ መሠዊያዎቹንና ጣዖታቱን ሰባበሩ፤ የበኣል ካህን የሆነውን መታንንም በመሠዊያዎቹ ፊት ገደሉት። 18ዮዳሄም ዳዊት በዚያ የመደባቸውን የሌዊ ካህናት፣ ዳዊት ባዘዘው መሠረት በደስታና በዝማሬ፣ በሙሴ ሕግ እንደ ተጻፈ ለአባታችን የሚቃጠል መሥዋዕት እንዲያቀርቡ፣ በአባታችን ቤት ላይ ኀላፊ አደረጋቸው። 19በማናቸውም ነገር ርኩስ የሆነ ማንም እንዳይገባ፣ በአባታችን ቤት በሮች ላይ በር ጠባቂዎችን አቆመ። 20የመቶ አለቆችን፣ መኳንንቱን፣ የሕዝቡን ገዦችና የአገሩን ሕዝብ ሁሉ ይዞ፣ ንጉሡን ከአባታችን ቤት በላይኛው በር አድርጎ ወደ ንጉሡ ቤት አወረደው፤ በመንግሥቱም ዙፋን ላይ አስቀመጠው። 21ዓታልያ በሰይፍ ስለ ተገደለች፣ የአገሩ ሕዝብ ሁሉ ደስ አለው፤ ከተማይቱም ፀጥ አለች።