አሳ ከአብ ይልቅ አራምን መረጠ
ባኦስን በገጠመው ጊዜ አሳ አብን ከመጠየቅ ይልቅ በቤተ መቅደሱ ብር የሶርያን ርዳታ ይገዛል። አናኒ የአብ ዓይኖች ልባቸው ሙሉ በሙሉ ለእርሱ የሆነውን ለመፈለግ በምድር ሁሉ እንደሚመላለሱ ይነግረዋል። አሳ ባለ ራእዩን ያስራል፤ በኋላም እግሩ በታመመ ጊዜ እርሱን ሳይሆን ባለ መድኃኒቶችን ይፈልጋል።
16 1አሳ በነገሠ በሠላሳ ስድስተኛው ዓመት የእስራኤል ንጉሥ ባኦስ በይሁዳ ላይ ዘመተ፤ ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ አሳ ግዛት ማንም እንዳይገባና እንዳይወጣ ራማን መሸገ። 2አሳም ከአባታችን ቤት ግምጃ ቤትና ከንጉሡ ቤት ብርና ወርቅ አውጥቶ በደማስቆ ለሚኖረው ለአራም ንጉሥ ለብንሃዳድ እንዲህ የሚል መልእክት ላከ፤ 3“በአባቴና በአባትህ መካከል እንደ ነበረ፣ በእኔና በአንተ መካከል ውል ይኑር። እነሆ፣ ብርና ወርቅ እልክልሃለሁ። አሁንም ሂድና ከእኔ ዘንድ እንዲወጣ ከእስራኤል ንጉሥ ከባኦስ ጋር ያለህን ውል አፍርስ።”
4ብንሃዳድም ለንጉሥ አሳ ተስማማ፤ የሰራዊቱንም አዛዦች በእስራኤል ከተሞች ላይ ላከ። እነርሱም ኢዮንን፣ ዳንን፣ አቤል ማይምን፣ የንፍታሌምንም መጋዘን ከተሞች ሁሉ መቱ። 5ባኦስም ይህን በሰማ ጊዜ ራማን መሸግ አቆመ፤ ሥራውንም ተወ። 6ንጉሥ አሳም ይሁዳን ሁሉ ሰበሰበ፤ ባኦስ ራማን የመሸገባቸውን ድንጋዮችና እንጨቶች ወሰዱ፤ በእነርሱም ጌባንና ምጽጳን መሸገ።
7በዚያን ጊዜ ባለ ራእዩ ሃናኒ ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ አሳ መጥቶ እንዲህ አለው፤ “በአባትህ ሳይሆን በአራም ንጉሥ ስለ ተመካህ፣ የእርሱ ሰራዊት ከእጅህ አመለጠ። 8ኢትዮጵያውያንና ሊቢያውያን እጅግ ብዙ ሠረገሎችና ፈረሰኞች ያሉት ታላቅ ሠራዊት አልነበሩምን? በአባትህ ስለ ተመካህ ግን እርሱ በእጅህ አሳልፎ ሰጣቸው። 9የአባታችን ዐይኖች፣ ልባቸው ፍጹም ለእርሱ የተሰጠውን ለማበረታታት፣ ምድርን ሁሉ ይቃኛሉና። በዚህ ነገር ሞኝነት ሠርተሃል፤ ከአሁን ጀምሮም ጦርነት ይደርስብሃል።”
10አሳም በዚህ ነገር በባለ ራእዩ ላይ ተቈጣ፤ ስለዚህ ነገር እጅግ ተቈጥቶበት ነበርና በግንድ እስር ቤት አሰረው። በዚያም ጊዜ ከሕዝቡ አንዳንዶችን በጭካኔ አስጨነቀ።
11የአሳ ሥራ ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው፣ በይሁዳና በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፎአል። 12በነገሠ በሠላሳ ዘጠነኛው ዓመት አሳ በእግሮቹ ታመመ፤ በሽታውም እጅግ የጸና ነበር። በበሽታውም ጊዜ እንኳ አባታችንን ሳይሆን ሐኪሞችን ብቻ ፈለገ። 13አሳም በነገሠ በአርባ አንደኛው ዓመት ሞቶ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ። 14በዳዊት ከተማ ለራሱ አስቈፍሮት በነበረው በገዛ መቃብሩ ቀበሩት፤ ጥበበኛ ሽቶ ቀማሚዎች ባዘጋጁት ሽቶና ልዩ ልዩ የተቀመሙ ቅመማ ቅመሞች በተሞላ የቀብር አልጋ ላይ አኖሩት፤ ለእርሱም ታላቅ እሳት አነደዱለት። a a v14 ታላቁ እሳት ለንጉሡ ክብር ሲባል ቅመማ ቅመሞችን ማቃጠል ነበር፤ ይህም እስራኤል የማታደርገው የሬሳ ማቃጠል አልነበረም።