አባታችን ከታማኝ ካልሆኑት ይርቃል
ካህናት፣ ንጉሥና ሕዝብ ሁሉ ተጠርተዋል። ሥራቸው እንዲመለሱ አይፈቅድላቸውም፤ በበጎቻቸውና በከብቶቻቸው ሊፈልጉት ሲሄዱም አብ ቀድሞ ፈቀቅ ብሏል። ለይሁዳ ብስባሽ፣ ለኤፍሬም አንበሳ መሆኑን ይናገራል፤ ከዚያም ጭንቀት መልሶ እስኪያመጣቸው ድረስ ትቷቸው ይሄዳል።
5 1ካህናት ሆይ፣ ይህን ስሙ! የእስራኤል ቤት ሆይ፣ አድምጡ! የንጉሡ ቤት ሆይ፣ አዳምጡ! ፍርዱ ለእናንተ የተወሰነ ነውና፣ በምጽጳ ወጥመድ፣ በታቦር ላይም የተዘረጋ መረብ ሆናችኋልና።
2“ዐመፀኞች በግድያ ጠልቀዋል፤ እኔ ግን ሁሉንም እቀጣቸዋለሁ። 3ኤፍሬምን አውቀዋለሁ፣ እስራኤልም ከእኔ የተሰወረ አይደለም፤ ኤፍሬም ሆይ፣ አሁን አመንዝረሃል፣ እስራኤልም ረክሷል።
4“ሥራቸው ወደ አባታቸው እንዲመለሱ አይፈቅድላቸውም፤ የዝሙት መንፈስ በውስጣቸው አለና፣ አባታችንንም አያውቁም። 5የእስራኤል ትዕቢት በእርሱ ላይ ይመሰክራል፤ እስራኤልና ኤፍሬም በኀጢአታቸው ይሰናከላሉ፤ ይሁዳም ከእነርሱ ጋራ ይሰናከላል። 6በበጎቻቸውና በከብቶቻቸው አባታችንን ሊፈልጉ ይሄዳሉ፣ ነገር ግን አያገኙትም፤ ከእነርሱ ርቋልና። 7ለአባታችን ታማኝ አልሆኑም፣ ዲቃላ ልጆችን ወልደዋልና። አሁን ሰርቀ ጨረቃ ከዕርሻቸው ጋራ ይበላቸዋል።
8“በጊብዓ ቀንድ ንፉ፣ በራማ መለከት ንፉ። በቤትዐዌን የጦር ድምፅ አሰሙ፤ ብንያም ሆይ፣ ወደ ኋላህ ተመልከት! 9ኤፍሬም በቅጣት ቀን ባድማ ይሆናል፤ በእስራኤል ነገዶች መካከል የተረጋገጠውን አስታውቃለሁ። 10የይሁዳ መሳፍንት የድንበር ድንጋይ እንደሚያፈልሱ ሆነዋል፤ ቍጣዬን እንደ ውሃ በእነርሱ ላይ አፈሳለሁ። 11ኤፍሬም ተጨቍኗል፣ በፍርድም ተቀጥቅጧል፤ ከንቱ ጣዖታትን ለመከተል ቈርጦ ነበርና። 12ስለዚህ ለኤፍሬም እንደ ብል፣ ለይሁዳም ቤት እንደ መበስበስ ነኝ።
13“ኤፍሬም በሽታውን አየ፣ ይሁዳም ቍስሉን አየ፤ ስለዚህ ኤፍሬም ወደ አሦር ሮጠ፣ ወደ ታላቁም ንጉሥ ተማጸነ። ያ ንጉሥ ግን ሊፈውስህ ወይም የሚመግለውን ቍስልህን ሊያድንልህ አይችልም። 14ለኤፍሬም እንደ አንበሳ፣ ለይሁዳም ቤት እንደ ደቦል አንበሳ እሆናለሁና። እኔው ራሴ ቀዳድጄ እሄዳለሁ፤ ተሸክሜ እወስዳለሁ፣ የሚያድንም አይኖርም። 15እንደ ገና ወደ ስፍራዬ እመለሳለሁ፤ በደላቸውን አምነው ፊቴን እስኪሹ ድረስ፤ በመከራቸው ትጋት ይፈልጉኛል።”