አባታችን ለሙሴ ይናገራል
በኩር ሁሉ የአብ ነው፤ በምትክ ይቤዣል፤ ልጁን ነጻ ለማውጣት የግብፅን በኩራት ወስዷልና። በዓሉና በእጅና በግንባር ላይ ያለው ምልክት የልጅ ጥያቄ መልስ እንዲያገኝ ነው። በደመናና በእሳት ፊት ፊታቸው እየሄደ በምድረ በዳው መንገድ ይመራቸዋል።
13 1አባታችን ሙሴን እንዲህ አለው፤
2“በኵርን ሁሉ ለእኔ ቀድስ፤ በእስራኤላውያን መካከል ማሕፀንን ከፍቶ የሚወጣ የመጀመሪያ ሁሉ፣ ሰው ይሁን እንስሳ፣ የእኔ ነው።” a a v2 አባታችን በኵርን ሁሉ የራሱ አድርጎ ይጠይቃል፤ ይህም ጥያቄ አብ ስለ እኛ በሰጠን በኵር በሆነው በኢየሱስ ፍጻሜውን ያገኛል።
3ሙሴም ሕዝቡን እንዲህ አላቸው፤ “ከግብፅ፣ ከባርነት ቤት የወጣችሁበትን ይህን ቀን አስታውሱ፤ አባታችን በብርቱ እጅ ከዚህ ስፍራ አውጥቷችኋልና። በእርሾ የተሠራ እንጀራ አትብሉ። 4ዛሬ፣ በአቢብ ወር፣ ትወጣላችሁ። 5አባታችን ወተትና ማር ወደሚፈስባት፣ ለአባቶቻችሁ ሊሰጣችሁ ወደ ማለላት ምድር፣ ወደ ከነዓናውያን፣ ወደ ኬጢያውያን፣ ወደ አሞራውያን፣ ወደ ኤዊያውያንና ወደ ኢያቡሳውያን አገር ባገባችሁ ጊዜ፣ ይህን ሥርዐት በዚህ ወር ጠብቁ። 6ሰባት ቀን ያልቦካ እንጀራ ትበላላችሁ፤ በሰባተኛውም ቀን ለአባታችን በዓል ይሆናል። 7ያልቦካ እንጀራ ሰባቱን ቀን ብሉ፤ በመካከላችሁ የቦካ እንጀራ አይገኝ፤ በዳር ድንበራችሁ ሁሉ እርሾ አይገኝ። 8በዚያም ቀን ልጅህን፣ ‘ይህ ከግብፅ በወጣሁ ጊዜ አባታችን ስለ እኔ ባደረገልኝ ነገር ምክንያት ነው’ ብለህ ንገረው። 9ይህም በእጅህ ላይ ምልክት፣ በግንባርህም ላይ ማስታወሻ ይሆንልሃል፤ የአባታችን ትምህርት በአፍህ እንዲሆን፤ አባታችን በብርቱ እጅ ከግብፅ አውጥቶሃልና። 10ስለዚህ ይህን ሥርዐት በተወሰነለት ጊዜ ከዓመት ዓመት ጠብቅ።
11አባታችን ላንተና ለአባቶችህ እንደ ማለላችሁ፣ ወደ ከነዓናውያን ምድር ባገባህና ለአንተ በሰጠህ ጊዜ፣ 12ማሕፀንን ከፍቶ የሚወጣውን ሁሉ ለአባታችን ለይ፤ የከብቶችህ በኵር ተባት ሁሉ የአባታችን ነው። 13የአህያ በኵር ሁሉ በበግ ተቤዠው፤ ባትቤዠው ግን አንገቱን ስበር። ከወንዶች ልጆችህ መካከል በኵርን ሁሉ ተቤዠው። 14ኋላም ልጅህ፣ ‘ይህ ምን ማለት ነው?’ ብሎ ሲጠይቅህ፣ እንዲህ ብለህ ንገረው፤ ‘አባታችን በብርቱ እጅ ከግብፅ፣ ከባርነት ቤት አወጣን። 15ፈርዖን እኛን ለመልቀቅ እልከኛ ሆኖ በእምቢታ በጸና ጊዜ፣ አባታችን በግብፅ ውስጥ ከሰው በኵር እስከ እንስሳ በኵር ድረስ፣ በኵር የሆነውን ሁሉ ገደለ። ስለዚህ እኔ ማሕፀንን ከፍቶ የሚወጣውን ተባት ሁሉ ለአባታችን እሠዋለሁ፤ የወንዶች ልጆችን በኵር ሁሉ ግን እቤዣለሁ።’” 16“ይህም በእጅህ ላይ ምልክት፣ በግንባርህም ላይ ማሰሪያ ይሆናል፤ አባታችን በብርቱ እጅ ከግብፅ አውጥቶናልና።”
ይበልጥ አስተማማኝ መንገድ
17ፈርዖን ሕዝቡን በለቀቀ ጊዜ፣ የፍልስጥኤማውያን ምድር መንገድ ቅርብ ቢሆንም እንኳ፣ አባታችን በዚያ መንገድ አልመራቸውም፤ አባታችን፣ “ሕዝቡ ጦርነት ቢገጥማቸው ሐሳባቸውን ለውጠው ወደ ግብፅ ይመለሱ ይሆናል” ብሎ ነበርና።
18ስለዚህ አባታችን ሕዝቡን በምድረ በዳ መንገድ ወደ ቀይ ባሕር አዙሮ መራቸው። እስራኤላውያንም ለጦርነት ተዘጋጅተው ከግብፅ ወጡ። b b v18 ዕብራይስጥ፦ ያም ሱፍ፣ “የሸምበቆ ባሕር”።
19ሙሴም የዮሴፍን አጥንቶች ወሰደ፤ ዮሴፍ የእስራኤልን ልጆች፣ “አባታችን በእርግጥ ይጐበኛችኋል፤ አጥንቶቼንም ከዚህ ከእናንተ ጋራ ይዛችሁ ታወጣላችሁ” ብሎ አምሎአቸው ነበርና። 20ከሱኮት ተነሥተው በምድረ በዳ ዳር በምትገኘው በኤታም ሰፈሩ። 21አባታችንም መንገድ ይመራቸው ዘንድ በቀን በደመና ዓምድ፣ ያበራላቸው ዘንድም በሌሊት በእሳት ዓምድ ሆኖ ቀድሟቸው ይሄድ ነበር፤ ስለዚህ ቀንም ሌሊትም መጓዝ ይችሉ ነበር። 22የቀኑ የደመና ዓምድና የሌሊቱ የእሳት ዓምድ ከሕዝቡ ፊት ከስፍራው ከቶ አልተለየም።