አብ ቤተ ሰቡን እንደሚመልስ ተስፋ ሰጠ
ለኋለኛው ትውልድ በመጽሐፍ የተጻፉ ቃላት። ሽብሩ እውነት ነው፤ ቍስሉም ከሰው መድኃኒት ሁሉ በላይ ነው፤ ነገር ግን የመታቸው አባታችን ራሱ እንደሚፈውሳቸው፣ ቀንበሩን ከአንገታቸው እንደሚሰብር፣ ዳግመኛም አባታቸው እንደሚሆን ቃል ይገባል።
30 1ከአባታችን ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣ ቃል፦
2የእስራኤል አባታችን እንዲህ ይላል፦ የነገርሁህን ቃሎች ሁሉ በመጽሐፍ ጻፍ። 3እነሆ፣ ቀኖች ይመጣሉ፤ ይላል አባታችን፤ በዚያም ጊዜ የሕዝቤን የእስራኤልንና የይሁዳን ምርኮ እመልሳለሁ፤ ይላል አባታችን፤ ለአባቶቻቸው ወደ ሰጠኋት ምድር እመልሳቸዋለሁ፤ እነርሱም ይወርሷታል።
4አባታችን ስለ እስራኤልና ስለ ይሁዳ የተናገራቸው ቃሎች እነዚህ ናቸው፦
5አባታችን እንዲህ ይላል፦ “የድንጋጤን ጩኸት ሰማን፤ ፍርሃት ነው እንጂ ሰላም የለም። 6አሁን ጠይቁና እዩ፤ ወንድ ይወልዳልን? ታዲያ ጎበዝ ሰው ሁሉ እንደ ምጥ እንደያዛት ሴት እጆቹን በወገቡ ላይ አድርጎ፣ ፊቱም ሁሉ ገርጥቶ የማየው ለምንድን ነው? 7ያ ቀን እንዴት የሚያስፈራ ነው! የሚመስለው የለም። ለያዕቆብ የመከራ ጊዜ ነው፤ ነገር ግን ከእርሱ ይድናል። 8በዚያ ቀን፣ ይላል የሰማይ ሠራዊት አባት፤ ቀንበሩን ከአንገትህ ላይ እሰብራለሁ፤ እስራትህንም እበጥሳለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲህ መጻተኞች ባሪያ አያደርጉትም። 9ይልቁንም አባታችንን፣ ንጉሣቸውንም ዳዊትን ያገለግላሉ፤ እርሱንም ለእነርሱ አስነሣዋለሁ። 10ስለዚህ አንተ ባሪያዬ ያዕቆብ ሆይ፣ አትፍራ፤ ይላል አባታችን፤ አንተም እስራኤል ሆይ፣ አትደንግጥ፤ እነሆ፣ ከሩቅ አድንሃለሁ፤ ልጆችህንም ከምርኮአቸው ምድር አድናለሁ። ያዕቆብ ወደ ዕረፍትና ወደ ሰላም ይመለሳል፤ የሚያስፈራውም የለም። 11እኔ ላድንህ ከአንተ ጋራ ነኝና፤ ይላል አባታችን። በመካከላቸው የበተንሁህን አሕዛብ ሁሉ ፈጽሜ ባጠፋም እንኳ፣ አንተን ግን ፈጽሜ አላጠፋህም፤ ነገር ግን በፍትሕ እቀጣሃለሁ፤ ያለ ቅጣትም ፈጽሜ አልተውህም።”
12አባታችን እንዲህ ይላልና፦ “ጉዳትህ የማይድን ነው፤ ቍስልህም የጸና ነው። 13ጕዳይህን የሚከራከርልህ የለም፤ ለቍስልህ መድኀኒት የለም፤ ፈውስም አይገኝልህም። 14ውሽሞችህ ሁሉ ረስተውሃል፤ ስለ አንተ ምንም አይገደዱም። በደልህ ታላቅ ስለ ሆነ፣ ኀጢአትህም ስለ በዛ፣ እንደ ጠላት ምት፣ በጨካኝ ሰው ቅጣት መትቼሃለሁ። 15ስለ ጕዳትህ ለምን ትጮኻለህ? ሕመምህ የማይድን ነው። በደልህ ታላቅ ስለ ሆነ፣ ኀጢአትህም ስለ በዛ፣ ይህን አደረግሁብህ። 16ስለዚህ የሚበሉህ ሁሉ ይበላሉ፤ ጠላቶችህም ሁሉ፣ እያንዳንዳቸው፣ ወደ ምርኮ ይሄዳሉ፤ የሚዘርፉህ ይዘረፋሉ፤ በአንተ ላይ የሚማርኩትን ሁሉ ለምርኮ አሳልፌ እሰጣለሁ።” 17ጤናሽን እመልሳለሁና፤ ቍስልሽንም እፈውሳለሁ፤ ይላል አባታችን፤ የተጣልሽ ብለው ጠርተውሻልና፦ “ይህች ጽዮን ናት፤ የሚሳሳላትም የለም።”
18አባታችን እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ የያዕቆብን ድንኳኖች ምርኮ እመልሳለሁ፤ ለመኖሪያዎቹም እራራለሁ፤ ከተማይቱ በፍርስራሽዋ ላይ ዳግም ትገነባለች፤ ቤተ መንግሥቱም በተገቢው ስፍራ ይቆማል። 19ከእነርሱም ምስጋናና የደስታ ድምፅ ይወጣል። አበዛቸዋለሁ፤ አያንሱም፤ አከብራቸዋለሁ፤ አይናቁም። 20ልጆቻቸው እንደ ቀድሞው ይሆናሉ፤ ማኅበራቸውም በፊቴ ይጸናል፤ የሚያስጨንቋቸውንም ሁሉ እቀጣለሁ። 21መሪያቸው ከእነርሱው አንዱ ይሆናል፤ ገዢያቸውም ከመካከላቸው ይወጣል። አቀርበዋለሁ፤ ወደ እኔም ይቀርባል፤ አለዚያ ወደ እኔ ለመቅረብ ነፍሱን ለአደጋ የሚያጋልጥ ማን ነውና? ይላል አባታችን። a a v21 ብቻውን ወደ አባታችን ይቀርብ ዘንድ የሚቀርበው ገዢ፣ ለልጆቹ ሁሉ ወደ አብ የሚወስደውን መንገድ ወደሚከፍተው ወደ ኢየሱስ ያመለክታል። 22እናንተም ልጆቼ ትሆናላችሁ፤ እኔም አባታችሁ እሆናለሁ።”
23እነሆ፣ የአባታችን ዐውሎ ነፋስ! ቍጣው ወጥቷል፤ ጠራጊ ዐውሎ ነፋስ ነው፤ በክፉዎች ራስ ላይ ይነጥቃል። 24የአባታችን የሚነድ ቍጣ የልቡን ዐሳብ ፈጽሞ እስኪፈጽም ድረስ አይመለስም። በሚመጡት ቀኖች ይህን ታስተውላላችሁ።