የአባታችን እንቈቅልሽ ስለ ሁለቱ ንስሮች
ስለ ሁለት ንስሮች፣ ስለ ዝግባ ጫፍና ስለ ተተከለ ወይን የቀረበ እንቆቅልሽ፣ ሴዴቅያስ ለባቢሎን የማለውን መሐላ አፍርሶ ፈረሶችን ለማግኘት ወደ ግብፅ እጁን እንደ ዘረጋ ተብሎ ተፈታ። ከዚህ አያመልጥም። ነገር ግን አብ የራሱን ለጋ ቀንበጥ በእስራኤል ተራራ ላይ እተክላለሁ አለ።
17 1የአባታችን ቃል ወደ እኔ መጣ፤
2“የሰው ልጅ ሆይ፤ ለእስራኤል ቤት እንቈቅልሽ አቅርብ፤ ምሳሌም ተናገር፤ 3እንዲህም በል፤ ጌታ አባታችን እንዲህ ይላል፤ ‘ትልቅ ክንፍ ያለው፣ ረዥም ላባ ያለውና በልዩ ልዩ ቀለም ያሸበረቀ ጕንጕን ያለው ታላቅ ንስር ወደ ሊባኖስ መጣ፤ የዝግባውንም ጫፍ ወሰደ። 4ከጫፍ ቀንበጦቹም አናት ላይ ያለውን ቈርጦ ወደ ንግድ ምድር ወሰደው፤ በነጋዴዎች ከተማም ውስጥ አኖረው። 5ከዚያም ከምድሪቱ ዘር ወስዶ በለም መሬት ተከለው፤ እንደ አኻያም ያድግ ዘንድ በብዙ ውሃ አጠገብ አኖረው። 6በቀለም፤ ዝቅ ብሎ የተንሰራፋ ወይን ሆነ፤ ቅርንጫፎቹ ወደ ንስሩ ዘወር አሉ፤ ሥሮቹም ከሥሩ ነበሩ። እንዲህም ወይን ሆነ፤ ቅርንጫፎችንም አወጣ፤ ቀንበጦችንም ሰደደ። 7ነገር ግን ትልቅ ክንፍና ብዙ ላባ ያለው ሌላ ታላቅ ንስር ነበረ፤ ይህም ወይን፣ ከተተከለበት መደብ ይልቅ ከእርሱ ብዙ ውሃ ይቀዳ ዘንድ ሥሮቹን ወደ እርሱ ጠመዘዘ፤ ቅርንጫፎቹንም ወደ እርሱ ዘረጋ። 8ቅርንጫፎችን ያበቅል፣ ፍሬም ያፈራ፣ ክቡርም ወይን ይሆን ዘንድ በብዙ ውሃ አጠገብ በመልካም መሬት ተተክሎ ነበር።’
9እንዲህ በል፤ ጌታ አባታችን እንዲህ ይላል፤ ‘ይለመልማልን? ሥሮቹን ነቅሎ ፍሬውን አያራግፍምን? አዲሶቹም ለምለም ቅጠሎቹ ሁሉ አይጠውልጉምን? ከሥሩ ነቅሎ ለማውጣት ኀያል ክንድ ወይም ብዙ ሕዝብ አያስፈልግም።’ 10‘ምንም እንኳ ቢተከል ይለመልማልን? የምሥራቅ ነፋስ በመታው ጊዜ ፈጽሞ አይጠውልግምን? ባደገበት መደብ ላይ አይደርቅምን?’”
11ከዚያም የአባታችን ቃል ወደ እኔ መጣ፤
12“ለዐመፀኛው ቤት እንዲህ በል፤ እነዚህ ነገሮች ምን ማለት እንደ ሆኑ አታውቁምን? እንዲህም ንገራቸው፤ ‘የባቢሎን ንጉሥ ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፤ ንጉሥዋንና ሹማምንቷን ወስዶ ወደ ባቢሎን አመጣቸው። 13ከንጉሣዊው ዘር አንዱን ወስዶ፣ በመሐላ ከእርሱ ጋር ኪዳን አደረገ፤ የአገሪቱንም ታላላቅ ሰዎች ማረከ፤ 14መንግሥቲቱ ተዋርዳ እንደ ገና እንዳትነሣ፤ ኪዳኑን በመጠበቅ ግን ጸንታ እንድትኖር ነው። 15ነገር ግን ሴዴቅያስ ፈረሶችንና ብዙ ሠራዊት ለማግኘት መልእክተኞችን ወደ ግብፅ ልኮ በባቢሎን ንጉሥ ላይ ዐመፀ። ይሳካለታልን? ይህን የሚያደርግ ያመልጣልን? ኪዳኑን አፍርሶ ያመልጣልን?’”
16ጌታ አባታችን እንዲህ ይላል፤ “ሕያው ነኝ! ያነገሠው ንጉሥ በሚኖርበት በባቢሎን ይሞታል፤ መሐላውን ንቋልና፣ ኪዳኑንም አፍርሷል። 17‘ፈርዖን ብዙ ነፍሳትን ለማጥፋት የመክበቢያ ዐፈር በሚከመርበትና የመክበቢያ ቅጥር በሚሠራበት ጊዜ፣ በኀይለኛ ሠራዊቱና በብዙ ጭፍራው በጦርነት አይረዳውም። 18መሐላውን ናቀ፤ ኪዳኑንም አፈረሰ፤ እጁን ሰጥቶ ሳለ ይህን ሁሉ ስላደረገ አያመልጥም።’”
19ስለዚህ ጌታ አባታችን እንዲህ ይላል፤ “ሕያው ነኝ! የናቀውን መሐላዬንና ያፈረሰውን ኪዳኔን በገዛ ራሱ ላይ አመጣለሁ። 20‘መረቤን በእርሱ ላይ እዘረጋለሁ፤ በወጥመዴም ይያዛል። ወደ ባቢሎን አመጣዋለሁ፤ በእኔ ላይ ስለ ፈጸመው ክህደት በዚያ እፈርድበታለሁ። 21ከጭፍሮቹ የተመረጡ ተዋጊዎች ሁሉ በሰይፍ ይወድቃሉ፤ የተረፉትም ወደ አራቱም ነፋስ ይበተናሉ። እኔም አባታችሁ እንደ ተናገርሁ ታውቃላችሁ።’”
22ጌታ አባታችን እንዲህ ይላል፤ “እኔ ራሴ ከዝግባው ከፍተኛ ጫፍ ቀንበጥ ወስጄ እተክላለሁ። ከጫፍ ቀንበጦቹም አናት ላይ ለስላሳ ቡቃያ ቈርጬ እኔ ራሴ ረዥምና ምጥቅ ባለ ተራራ ላይ እተክለዋለሁ። a a v22 የሰው መንግሥታት በሚከሽፉበት ስፍራ፣ አባታችን የራሱን ለስላሳ ቡቃያ ለመትከል ተስፋ ይሰጣል፤ ይኸውም ከዳዊት ዘር የሚመጣው ንጉሥ ነው፤ በኢየሱስም ተፈጸመ፤ እርሱም ሕዝቦችን ሁሉ የሚያስጠልል መንግሥት እስኪሆን ድረስ ያድጋል። 23በእስራኤል ተራራ ከፍታ ላይ እተክለዋለሁ፤ ቅርንጫፎችንም ያወጣል፤ ፍሬም ያፈራል፤ ክቡርም ዝግባ ይሆናል። የወፍ ዝርያ ሁሉ ከሥሩ ይኖራል፤ በቅርንጫፎቹም ጥላ ሥር ጎጆ ይሠራል። 24የሜዳ ዛፎችም ሁሉ፣ ረዥሙን ዛፍ ዝቅ የማደርግ፣ ዝቅተኛውንም ዛፍ ከፍ የማደርግ፣ ለምለሙን ዛፍ የማደርቅ፣ የደረቀውንም ዛፍ የማለመልም እኔ አብ እንደ ሆንሁ ያውቃሉ። እኔ አብ ተናግሬአለሁ፤ አደርገዋለሁም።”