የኢያቦስቴ መገደል
ሁለት የኢያቡስቴ የራሱ የወራሪ ጭፍራ አለቆች በቀትር ዕረፍቱ በአልጋው ላይ ወግተው ይገድሉታል፤ ራሱንም የአብ በቀል ብለው ወደ ኬብሮን ይወስዳሉ። ቀድሞ ሳኦልን ገደልሁ ያለውን ሰው የገደለው ዳዊት እነርሱንም ያስገድላቸዋል። ራሱም በአበኔር መቃብር ይቀበራል።
4 1የሳኦል ልጅ ኢያቦስቴ አበኔር በኬብሮን መሞቱን በሰማ ጊዜ ልቡ ፈራ፤ እስራኤልም ሁሉ ተደናገጠ። 2የሳኦል ልጅ ሁለት የወራሪ ጭፍራ አለቆች ነበሩት፤ እነርሱም ከብንያም ነገድ የሆኑት የቤሮታዊው የሬሞን ልጆች ባናና ሬካብ ነበሩ፤ ቤሮትም ደግሞ የብንያም ክፍል ሆና ትቈጠራለችና፤ 3ቤሮታውያን ወደ ጊታይም ሸሽተው እስከ ዛሬ ድረስ በዚያ እንደ መጻተኛ ኖረዋልና።
4የሳኦል ልጅ ዮናታን ሁለቱም እግሮቹ የሰለሉ ልጅ ነበረው። ስለ ሳኦልና ስለ ዮናታን ወሬ ከይዝራኤል በመጣ ጊዜ ዕድሜው አምስት ዓመት ነበር፤ ሞግዚቱም ልትሸሽ ይዛው ስትቸኩል ወደቀና ሰለለ። ስሙም ሜምፊቦስቴ ነበር።
5የቤሮታዊው የሬሞን ልጆች ሬካብና ባና በቀትር ትኵሳት ኢያቦስቴ የቀትር ዕረፍቱን ሲያርፍ ወደ ቤቱ መጡ። 6ስንዴ ሊወስዱ ያህል ወደ ቤቱ መካከል ገብተው ሆዱን ወጉት፤ ሬካብና ወንድሙ ባናም አመለጡ። 7ኢያቦስቴ በመኝታ ክፍሉ በአልጋው ላይ ተኝቶ ሳለ ወደ ቤቱ ገብተው ነበር። መትተው ገደሉት፤ ራሱንም ቈርጠው ወስደው ሌሊቱን ሁሉ በአራባ መንገድ ተጓዙ። 8የኢያቦስቴንም ራስ ወደ ኬብሮን ወደ ዳዊት አምጥተው ንጉሡን እንዲህ አሉት፤ “እነሆ፣ ነፍስህን ይፈልግ የነበረው የጠላትህ የሳኦል ልጅ የኢያቦስቴ ራስ ይህ ነው። ዛሬ አባታችን ለጌታዬ ለንጉሡ ከሳኦልና ከዘሩ በቀል ተበቀለ።” a a v8 ገዳዮቹ ወንጀላቸውን ለአባታችን ይሰጣሉ፤ ነገር ግን መልሱ ንጹሕ ሰውን እንደ ገደሉ ነፍሰ ገዳዮች አድርጎ በሚፈርድባቸው በዳዊት በኩል ይመጣል።
9ዳዊት ግን የቤሮታዊው የሬሞን ልጆች ሬካብንና ወንድሙን ባናን እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “ነፍሴን ከመከራ ሁሉ የዋጀ አባታችን በሕይወት እንዳለ፣ 10አንድ ሰው ‘እነሆ ሳኦል ሞቷል’ ብሎ የምሥራች ያመጣ መስሎት በነገረኝ ጊዜ፣ በጺቅላግ ይዤ ገደልሁት፤ ለዜናው የከፈልሁት ዋጋ ይህ ነበር! 11ክፉ ሰዎች ጻድቅን ሰው በገዛ ቤቱ በራሱ አልጋ ላይ ሲገድሉ፣ ይልቁንስ አሁን ደሙን ከእጃችሁ ፈልጌ ከምድር ላይ አላስወግዳችሁምን? 12ዳዊትም ጕልማሶቹን አዘዘ፤ እነርሱም ገደሏቸው፤ እጆቻቸውንና እግሮቻቸውንም ቈርጠው ሬሳቸውን በኬብሮን ባለው ኵሬ አጠገብ ሰቀሉ። የኢያቦስቴን ራስ ግን በኬብሮን በአበኔር መቃብር ቀበሩት።”