በእስራኤል አባት የለምን?
እስራኤልና ይሁዳ ቀስ በቀስ ወድቀው ወደ ምርኮ የሚሄዱበት ረጅም ጉዞ። ፍርድ በሚወርድበት ጊዜ እንኳ፣ መጽሐፉ ልጆቹን አሳልፎ ለመስጠት የማይቸኩለውን አብ ደጋግሞ በጨረፍታ ያሳያል።
1 1አክዓብ ከሞተ በኋላ፣ ሞዓብ በእስራኤል ላይ ዐመፀ።
2አካዝያስ በሰማርያ ባለው የሰገነቱ መስኮት መቃን ውስጥ ወድቆ ቈሰለ። መልእክተኞችንም ልኮ፣ “ሄዳችሁ የዔቅሮንን አምላክ ብዔልዜቡብን ከዚህ ጕዳት እድን እንደ ሆነ ጠይቁ” አላቸው።
3ነገር ግን የአባታችን መልአክ ቴስብያዊውን ኤልያስን እንዲህ አለው፤ “ተነሥተህ የሰማርያውን ንጉሥ መልእክተኞች ተገናኝተህ፣ ‘የዔቅሮንን አምላክ ብዔልዜቡብን ልትጠይቁ የምትሄዱ በእስራኤል አባት የለምን?’ ብለህ ጠይቃቸው።
4ስለዚህ አባታችን እንዲህ ይላል፤ ‘ከወጣህበት አልጋ አትወርድም፤ በእርግጥ ትሞታለህ።’” ኤልያስም ሄደ።
5መልእክተኞቹ ወደ ንጉሡ በተመለሱ ጊዜ፣ “ለምን ተመለሳችሁ?” አላቸው።
6እነርሱም እንዲህ ብለው መለሱ፤ “አንድ ሰው ሊገናኘን መጥቶ እንዲህ አለን፤ ‘ወደ ላካችሁ ንጉሥ ተመልሳችሁ እንዲህ በሉት፤ አባታችን እንዲህ ይላል፤ የዔቅሮንን አምላክ ብዔልዜቡብን ልትጠይቁ ሰዎች የምትልኩ በእስራኤል አባት የለምን? ስለዚህ ከወጣህበት አልጋ አትወርድም፤ በእርግጥ ትሞታለህ።’”
7ንጉሡም፣ “ይህን ነግሯችሁ ሊገናኛችሁ የመጣው ሰው ምን ዐይነት ነበር?” ብሎ ጠየቀ።
8እነርሱም፣ “ጠጕር ያለው ልብስ ለብሶ፣ በወገቡ ላይ የቈዳ መታጠቂያ ታጥቆ ነበር” አሉት። ንጉሡም፣ “ቴስብያዊው ኤልያስ ነው” አለ።
9ንጉሡም የኀምሳ አለቃን ከኀምሳ ሰዎቹ ጋራ ወደ ኤልያስ ላከ። አለቃውም ኤልያስ በኰረብታው ራስ ተቀምጦ ሳለ ወደ እርሱ ወጥቶ፣ “የአባታችን ሰው ሆይ፣ ንጉሡ፣ ‘ውረድ’ ይልሃል” አለው።
10ኤልያስም ለአለቃው መልሶ፣ “እኔ የአባታችን ሰው ከሆንሁ፣ ከሰማይ እሳት ወርዶ አንተንና ኀምሳዎችህን ይበላ” አለ። ከሰማይም እሳት ወርዶ እርሱንና ኀምሳ ሰዎቹን በላ።
11ንጉሡም እንደ ገና ሌላ የኀምሳ አለቃን ከኀምሳ ሰዎች ጋራ ላከ፤ እርሱም፣ “የአባታችን ሰው ሆይ፣ ንጉሡ፣ ‘ፈጥነህ ውረድ’ ይልሃል” አለ።
12ኤልያስም መልሶ፣ “እኔ የአባታችን ሰው ከሆንሁ፣ ከሰማይ እሳት ወርዶ አንተንና ኀምሳዎችህን ይበላ” አለ። የአባታችንም እሳት ከሰማይ ወርዶ እርሱንና ኀምሳ ሰዎቹን በላ።
13ንጉሡም ሦስተኛውን የኀምሳ አለቃ ከኀምሳ ሰዎቹ ጋራ ላከ። ይህም አለቃ ወጥቶ በኤልያስ ፊት ተንበርክኮ እንዲህ ብሎ ለመነው፤ “የአባታችን ሰው ሆይ፣ እባክህ ነፍሴና የእነዚህ የኀምሳ ባሪያዎችህ ነፍስ በፊትህ ክቡር ይሁኑ። 14ከሰማይ እሳት ወርዶ ሁለቱን የቀድሞ አለቆች ከኀምሳ ሰዎቻቸው ጋራ በልቷል። አሁን ግን ነፍሴ በፊትህ ክቡር ይሁን።”
15የአባታችንም መልአክ ኤልያስን፣ “ከእርሱ ጋራ ውረድ፤ አትፍራው” አለው። ስለዚህ ኤልያስ ከእርሱ ጋራ ወደ ንጉሡ ወረደ።
16ንጉሡንም እንዲህ አለው፤ “አባታችን እንዲህ ይላል፤ የዔቅሮንን አምላክ ብዔልዜቡብን ልትጠይቅ መልእክተኞችን ላክህ፤ ቃሉን ልትጠይቅ በእስራኤል አባት የለምን? ስለዚህ ከወጣህበት አልጋ አትወርድም፤ በእርግጥ ትሞታለህ።”
17አካዝያስም አባታችን በኤልያስ በኩል በተናገረው ቃል መሠረት ሞተ። አካዝያስ ወንድ ልጅ ስላልነበረው፣ በይሁዳ ንጉሥ በኢዮሣፍጥ ልጅ በኢዮራም በሁለተኛው ዓመት፣ ኢዮራም በእርሱ ፋንታ ነገሠ። 18የአካዝያስም ሌሎች ሥራዎች፣ ያደረገው ሁሉ፣ በእስራኤል ነገሥታት ዜና መዋዕል መጽሐፍ ተጽፈው የሉምን?