ሕዝቅያስ የአብን ቤት አነጻ
ሕዝቅያስ በመጀመሪያው ወሩ አባቱ የዘጋቸውን ደጆች ይከፍታል፣ ሌዋውያንም ርኵሰቱን ከመቅደሱ እንዲያወጡ ያደርጋል። መሥዋዕቶች፣ ጸናጽል፣ በገናና መለከት ይመለሳሉ፤ የአብ ቤት አገልግሎትም ይታደሳል — በድንገት፣ ለሁሉም ደስታ።
29 1ሕዝቅያስ በሃያ አምስት ዓመቱ ነገሠ፤ በኢየሩሳሌምም ሃያ ዘጠኝ ዓመት ነገሠ። እናቱ የዘካርያስ ልጅ አብያ ትባል ነበር። 2አባቱ ዳዊት እንዳደረገው ሁሉ፣ በአባታችን ዐይን ፊት መልካሙን አደረገ። 3በነገሠ በመጀመሪያው ዓመት በመጀመሪያው ወር የአባታችንን ቤት በሮች ከፈተ፤ ጠገናቸውም። 4ካህናትንና ሌዋውያንን አስገባ፤ በምሥራቅም በኩል ባለው አደባባይ ሰበሰባቸው። 5እንዲህም አላቸው፤ “ሌዋውያን ሆይ፣ ስሙኝ! አሁን ራሳችሁን ቀድሱ፤ የአባቶቻችሁ አምላክ የሆነውን የአባታችንን ቤት ቀድሱ፤ ከቅዱሱ ስፍራም ርኩሰቱን አስወግዱ። 6አባቶቻችን ታማኝ አልነበሩም፤ በአባታችን ዐይን ፊት ክፉውን አደረጉ፤ ተዉት፤ ፊታቸውንም ከአባታችን ማደሪያ መለሱ፤ ጀርባቸውንም ሰጡ። 7ደግሞም የመመላለሻውን አዳራሽ በሮች ዘጉ፤ መብራቶቹንም አጠፉ፤ በመቅደሱም ውስጥ ለእስራኤል አምላክ ለአባታችን ዕጣን አላጠኑም፤ የሚቃጠል መሥዋዕትም አላቀረቡም። 8ስለዚህ የአባታችን ቍጣ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ ወረደ፤ በገዛ ዐይናችሁ እንደምታዩት፣ የድንጋጤ፣ የፍርሃትና የመሳለቂያ ነገር አደረጋቸው። 9አባቶቻችን በሰይፍ ወድቀዋልና፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችን፣ ሚስቶቻችንም ስለዚህ ተማርከዋል። 10አሁንም የመዓቱ ጽናት ከእኛ እንዲመለስ፣ ከእስራኤል አምላክ ከአባታችን ጋራ ኪዳን ለመግባት አስቤአለሁ። 11ልጆቼ ሆይ፣ አሁን ቸል አትበሉ፤ አባታችን በፊቱ ልትቆሙ፣ ልታገለግሉት፣ አገልጋዮቹም ልትሆኑ ዕጣንም ልታጥኑ መርጦአችኋልና።”
12ሌዋውያኑም ተነሡ፤ ከቀዓታውያን የአማሳይ ልጅ ማሃት፣ የአዛርያም ልጅ ኢዮኤል፤ ከመረራውያን የዓብዲ ልጅ ቂስ፣ የይሃልኤልም ልጅ አዛርያ፤ ከጌድሶናውያን የዚማ ልጅ ኢዮሐ፣ የኢዮሐም ልጅ ዔድን፤ 13ከኤሊሳፋን ልጆች ሽምሪና ይዕኤል፤ ከአሳፍ ልጆች ዘካርያስና መጣንያ፤ 14ከሔማን ልጆች ይሒኤልና ሽሚ፤ ከይዱቱን ልጆችም ሸማያና ዑዝኤል። 15ወንድሞቻቸውን ሰበሰቡ፤ ራሳቸውንም ቀደሱ፤ ንጉሡም በአባታችን ቃል እንዳዘዘ፣ የአባታችንን ቤት ለማንጻት ገቡ። 16ካህናቱም ሊያነጹት ወደ አባታችን ቤት ውስጠኛ ክፍል ገቡ፤ በአባታችንም መቅደስ ያገኙትን ርኩሰት ሁሉ ወደ አደባባዩ አወጡት፤ ሌዋውያኑም ወደ ቄድሮን ወንዝ ወሰዱት። 17በመጀመሪያው ወር በመጀመሪያው ቀን መቀደስ ጀመሩ፤ በወሩም በስምንተኛው ቀን የአባታችን መመላለሻ አዳራሽ ደረሱ፤ የአባታችንንም ቤት ስምንት ቀን ቀደሱ፤ በመጀመሪያው ወር በዐሥራ ስድስተኛው ቀንም ፈጸሙ። 18ከዚያም ወደ ንጉሥ ሕዝቅያስ ገብተው እንዲህ አሉ፤ “የአባታችንን ቤት በሙሉ አነጻን፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕት መሠዊያ ከዕቃዎቹ ሁሉ ጋራ፣ የገጸ ኅብስቱንም ጠረጴዛ ከዕቃዎቹ ሁሉ ጋራ አነጻን። a a v18 የገጸ ኅብስት፤ በእግዚአብሔር ፊት እንደ ዘውታሪ ቍርባን ሆኖ በቅዱሱ ስፍራ ባለ ልዩ ጠረጴዛ ላይ የሚቀመጥ ዐሥራ ሁለት እንጀራ ነው። 19ንጉሥ አካዝ በነገሠበትና ታማኝ ባልሆነበት ዘመን የጣላቸውን ዕቃዎች ሁሉ አዘጋጅተን ቀድሰናል፤ እነሆ፣ በአባታችን መሠዊያ ፊት ቆመዋል።”
አምልኮ ወደ አብ ቤት ተመለሰ
20ንጉሥ ሕዝቅያስም ማልዶ ተነሣ፤ የከተማዪቱንም መኳንንት ሰበሰበ፤ ወደ አባታችን ቤትም ወጣ። 21ለመንግሥቱ፣ ለመቅደሱና ለይሁዳ የኀጢአት መሥዋዕት እንዲሆኑ ሰባት ወይፈኖች፣ ሰባት አውራ በጎች፣ ሰባት ጠቦቶች፣ ሰባት አውራ ፍየሎች አመጡ፤ የአሮን ልጆች የሆኑትንም ካህናት በአባታችን መሠዊያ ላይ እንዲያቀርቡአቸው አዘዛቸው። 22ወይፈኖቹንም አረዱ፤ ካህናቱም ደሙን ወስደው በመሠዊያው ላይ ረጩት፤ አውራ በጎቹንም አረዱ፤ ደሙንም በመሠዊያው ላይ ረጩት፤ ጠቦቶቹንም አረዱ፤ ደሙንም በመሠዊያው ላይ ረጩት። 23የኀጢአት መሥዋዕት የሆኑትን ፍየሎች በንጉሡና በጉባኤው ፊት አቀረቡ፤ እጆቻቸውንም በእነርሱ ላይ ጫኑ። 24ካህናቱም አረዱአቸው፤ ለእስራኤልም ሁሉ ማስተስረያ እንዲሆን ደማቸውን በመሠዊያው ላይ የኀጢአት መሥዋዕት አድርገው አቀረቡ፤ ንጉሡ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የኀጢአትን መሥዋዕት ለእስራኤል ሁሉ እንዲሆን አዝዞ ነበርና።
25ዳዊት፣ የንጉሡ ባለ ራእይ ጋድና ነቢዩ ናታን እንዳዘዙ፣ ሌዋውያኑን ከጸናጽል፣ ከበገናና ከመሰንቆ ጋራ በአባታችን ቤት አቆማቸው፤ ትእዛዙ ከአባታችን በነቢያቱ በኩል መጥቶ ነበርና። 26ሌዋውያኑም በዳዊት የሙዚቃ መሣሪያዎች፣ ካህናቱም በመለከቶች ቆሙ። 27ሕዝቅያስም የሚቃጠለውን መሥዋዕት በመሠዊያው ላይ እንዲቀርብ አዘዘ፤ መሥዋዕቱም በጀመረ ጊዜ፣ ከመለከቶችና ከእስራኤል ንጉሥ ከዳዊት የሙዚቃ መሣሪያዎች ጋራ የአባታችን መዝሙር ደግሞ ተጀመረ። 28የሚቃጠለው መሥዋዕት እስኪፈጸም ድረስ፣ ጉባኤው ሁሉ ሰገደ፤ ዘማሪዎቹም ዘመሩ፤ መለከት ነፊዎቹም ነፉ።
29መሥዋዕቱም ባለቀ ጊዜ፣ ንጉሡና ከእርሱ ጋራ የነበሩ ሁሉ ተደፍተው ሰገዱ። 30ንጉሥ ሕዝቅያስና መኳንንቱም ሌዋውያኑ በዳዊትና በባለ ራእዩ በአሳፍ ቃል አባታችንን እንዲያመሰግኑ አደረጉ፤ በደስታም ዘመሩ፤ ዝቅ ብለውም ሰገዱ፤ አመለኩም።
31ከዚያም ሕዝቅያስ እንዲህ አለ፤ “አሁን ራሳችሁን ለአባታችን ቀድሳችኋል፤ ቅረቡ፤ መሥዋዕትና የምስጋና ቍርባን ወደ አባታችን ቤት አምጡ።” ጉባኤውም መሥዋዕትና የምስጋና ቍርባን አመጣ፤ ልባቸው ፈቃደኛ የሆኑ ሁሉም የሚቃጠል መሥዋዕት አመጡ። 32ጉባኤው ያመጣው ሰባ ወይፈኖች፣ መቶ አውራ በጎች፣ ሁለት መቶ ጠቦቶች ነበሩ፤ እነዚህ ሁሉ ለአባታችን የሚቃጠል መሥዋዕት ነበሩ። 33የተቀደሱትም ቍርባኖች ስድስት መቶ ወይፈኖችና ሦስት ሺህ በጎች ነበሩ። 34ካህናቱ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ሁሉ ለማለጥ ጥቂቶች ነበሩ፤ ስለዚህ የሌዋውያን ወንድሞቻቸው ሥራው እስኪፈጸምና ካህናቱም ራሳቸውን እስኪቀድሱ ድረስ ረዷቸው፤ ሌዋውያኑ ራሳቸውን በመቀደስ ከካህናቱ ይልቅ በልባቸው ቅን ነበሩና። 35ከብዙዎቹ ከሚቃጠሉ መሥዋዕቶች ሌላ፣ ከደኅንነት መሥዋዕቶች የተገኘ ስብና ለእነርሱም የሚቀርብ የመጠጥ ቍርባን ነበረ፤ እንዲሁም የአባታችን ቤት አገልግሎት ዳግመኛ ተመለሰ። 36ነገሩ በድንገት ስለ ሆነ፣ ሕዝቅያስና ሕዝቡ ሁሉ አባታችን ላዘጋጀላቸው ነገር ደስ አላቸው።