የመርዶክዮስ ታላቅነት
በንጉሣዊ ዜና መዋዕል ስልት የተጻፈ የሦስት ቁጥሮች መዝጊያ ማስታወሻ፦ ንጉሡ በምድሩና በባሕር ዳርቻዎች ላይ ግብር ይጥላል፤ ከዙፋኑ ቀጥሎ ሁለተኛ የሆነው መርዶክዮስም ያንን ሥልጣን የሕዝቡን መልካም ለመሻትና ለወገኑ ሁሉ ሰላምን ለመናገር በመጠቀሙ ይታወሳል።
10 1ንጉሡ ጠረክሲስ በምድሪቱና በባሕር ዳር አገሮች ላይ ግብር ጣለ። 2ያደረጋቸው የኀይልና የብርታት ሥራዎቹ ሁሉ፣ ንጉሡም መርዶክዮስን ከፍ ከፍ ያደረገበት የታላቅነቱ ሙሉ ዘገባ በሜዶንና በፋርስ ነገሥታት የዜና መዋዕል መጽሐፍ ተጽፈው የሉምን? 3አይሁዳዊው መርዶክዮስ ከንጉሡ ከጠረክሲስ ቀጥሎ ሁለተኛ ሆነ፤ በአይሁድ መካከል ታላቅ፣ በብዙ ወንድሞቹ ዘንድ የተወደደ፣ የወገኖቹን ደኅንነት የሚሻ፣ ለዘሩ ሁሉ ሰላምን የሚናገር ነበር።