እስራኤል ጣዖትን ሁሉ አፈረሰ
በዓሉ ሕዝቡ ሐውልቶቹንና የኮረብታ መስገጃዎቹን ለማፍረስ በመውጣቱ ይፈጸማል። ከዚያም አሥራቱ እጅግ ተትረፍርፎ ስለሚገባ ክምር ሆኖ ይቆማል፣ ግምጃ ቤቶች መሠራት ያስፈልጋቸዋል፣ ካህናቱና ሌዋውያኑም ራሳቸውን ለአብ ሕግ እንዲሰጡ ክፍፍሉ በየስማቸው ይደራጃል።
31 1ይህ ሁሉ ባለቀ ጊዜ፣ በዚያ የነበሩት እስራኤላውያን ሁሉ ወደ ይሁዳ ከተሞች ወጥተው የማምለኪያ ዐምዶችን ሰባበሩ፤ የአሼራ ምሰሶዎችን ቈረጡ፤ በይሁዳ፣ በብንያም፣ በኤፍሬምና በምናሴ ሁሉ የነበሩትን የኰረብታ መስገጃዎችንና መሠዊያዎችን ፈጽመው እስኪያጠፉ ድረስ አፈረሱ። ከዚያም እስራኤላውያን ሁሉ እያንዳንዳቸው ወደ ርስታቸው፣ ወደ ከተሞቻቸው ተመለሱ።
2ሕዝቅያስ ካህናትንና ሌዋውያንን እያንዳንዳቸውን እንደ አገልግሎታቸው፣ ካህናቱንም ሌዋውያኑንም በየክፍላቸው መደበ፤ ይኸውም የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት ለማቅረብ፣ በአባታችን ሰፈሮች ደጆችም ለማገልገል፣ ምስጋና ለማቅረብና ለማወደስ ነበር።
3ንጉሡም ለሚቃጠለው መሥዋዕት ከራሱ ሀብት ሰጠ፤ ይኸውም የጥዋትና የማታ የሚቃጠል መሥዋዕት፣ እንዲሁም በአባታችን ሕግ እንደ ተጻፈ ለሰንበቶች፣ ለመባቻዎችና ለተወሰኑ በዓላት የሚቀርበው መሥዋዕት ነበር። 4በኢየሩሳሌምም ለሚኖሩት ሰዎች ራሳቸውን ለአባታችን ሕግ መስጠት እንዲችሉ የካህናቱንና የሌዋውያኑን ድርሻ እንዲሰጡ አዘዛቸው። 5ትእዛዙም እንደ ተሰራጨ፣ እስራኤላውያን የእህልን፣ የወይን ጠጅን፣ የዘይትን፣ የማርንና የዕርሻን ፍሬ ሁሉ በኵራት በብዛት ሰጡ፤ የሁሉንም ነገር ዐሥራት በብዛት አመጡ። 6በይሁዳ ከተሞችም የሚኖሩት እስራኤላውያንና ይሁዳውያን ደግሞ የከብትንና የበግን ዐሥራት፣ እንዲሁም ለአባታችን የተቀደሰውን ነገር ዐሥራት አምጥተው ክምር ክምር አድርገው ከመሩ።
7ክምሩንም መከመር የጀመሩት በሦስተኛው ወር ሲሆን፣ የጨረሱትም በሰባተኛው ወር ነበር። a a v7 ሦስተኛው ወር በግንቦት መጨረሻ–ሰኔ ላይ ይውላል፤ ሰባተኛው ወር ደግሞ በመስከረም–ጥቅምት ይውላል፤ ይህም ወደ አራት ወር የሚጠጋ የስጦታ ጊዜ ነው። 8ሕዝቅያስና ሹማምቱም መጥተው ክምሩን አዩ፤ አባታችንንና ሕዝቡን እስራኤልንም ባረኩ። 9ሕዝቅያስም ካህናቱንና ሌዋውያኑን ስለ ክምሩ ጠየቃቸው። 10ከሳዶቅ ቤት የሆነው ሊቀ ካህናቱ አዛርያስም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “ሰዎች መባውን ወደ አባታችን ቤት ማምጣት ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ፣ በልተን ጠግበናል፤ የተረፈውም ብዙ ነው፤ ምክንያቱም አባታችን ሕዝቡን ባርኮአልና ይህ ታላቅ ትርፍ ተረፈ።”
11ከዚያም ሕዝቅያስ በአባታችን ቤት ውስጥ መጋዘኖችን እንዲያዘጋጁ አዘዛቸው፤ እነርሱም አዘጋጁ። 12መባውንም፣ ዐሥራቱንና የተቀደሱትን ስጦታዎች በታማኝነት አስገቡ። ሌዋዊው ኮናንያስ አለቃቸው ነበር፤ ወንድሙ ሳሚም ሁለተኛው ነበር። 13ይሒኤል፣ አዛዝያስ፣ ናሃት፣ አሳሄል፣ ይሪሞት፣ ዮዛባድ፣ ኤሊኤል፣ ይስማክያስ፣ ማሃትና በናያስ በኮናንያስና በወንድሙ በሳሚ ሥር ተቈጣጣሪዎች ነበሩ፤ እነርሱም በንጉሥ ሕዝቅያስና የአባታችን ቤት የበላይ ሹም በሆነው በአዛርያስ የተሾሙ ነበሩ። 14ወደ ምሥራቅ በኩል የነበረው የሌዋዊው በረኛ የይምናህ ልጅ ቆሬ፣ ለአባታችን የሚቀርበውን የፈቃድ መባ ይቈጣጠር ነበር፤ የአባታችንንም መባና እጅግ የተቀደሱትን ስጦታዎች ያከፋፍል ነበር። 15ከእርሱም በታች ዔደን፣ ሚንያሚን፣ ኢያሱ፣ ሸማያስ፣ አማርያስና ሰካንያስ በካህናቱ ከተሞች በታማኝነት ያገለግሉ ነበር፤ ለታላቁም ለታናሹም ለባልንጀሮቻቸው ካህናት በየክፍላቸው ያከፋፍሉ ነበር፤ 16ከዚህም ሌላ በትውልድ ሐረግ ለተመዘገቡት፣ ዕድሜያቸው ከሦስት ዓመትና ከዚያ በላይ ለሆኑት ወንዶች ሁሉ ይሰጡ ነበር፤ እነዚህም የዕለት ተዕለት ተግባራቸውን ለመፈጸም ወደ አባታችን ቤት የሚገቡት ሁሉ ነበሩ፤ ይኸውም እንደ ሥራቸውና እንደ ክፍላቸው ለአገልግሎታቸው ነበር። 17ካህናቱም እንደ ነገዳቸው ተመዘገቡ፤ ሌዋውያኑም ዕድሜያቸው ከሃያ ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑት እንደ ተግባራቸውና እንደ ክፍላቸው ተመዘገቡ። 18ከሕፃናታቸው፣ ከሚስቶቻቸው፣ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆቻቸው ሁሉ ጋራ ተመዘገቡ፤ ይኸውም መላው ማኅበር ነበር፤ ምክንያቱም ራሳቸውን በቅድስና በታማኝነት ለይተው ቀድሰው ነበር። 19በከተሞቻቸው ዙሪያ ባሉት የግጦሽ ሜዳዎች ለሚኖሩት ለአሮን ዘሮች ለሆኑት ካህናት፣ ለወንድ ካህናት ሁሉና በትውልድ ሐረግ ለተመዘገቡት ሌዋውያን ሁሉ ድርሻ እንዲሰጡ በየከተማይቱ ሁሉ ሰዎች በስም ተመደቡ።
20ሕዝቅያስም በይሁዳ ሁሉ ይህን አደረገ። በአባታችንም ፊት መልካሙን፣ ቅኑንና ታማኙን አደረገ። 21በጀመረውም ሥራ ሁሉ—የአባታችንን ቤት በማገልገል፣ ሕግንና ትእዛዝን በመጠበቅ፣ አባታችንንም በመፈለግ—በሙሉ ልቡ ሠራ፤ ተከናወነለትም።