አባታችን ሐሰተኛ ነቢይን ያጋልጣል
ሐናንያ የባቢሎን ቀንበር በሁለት ዓመት ውስጥ እንደሚሰበር በሕዝብ ፊት ያውጃል፤ ለማረጋገጥም የኤርምያስን የቀንበር ዘንግ ይሰብራል። ኤርምያስ «አሜን» ብሎ ይመልሳል፤ ከዚያም በእንጨት ፋንታ የአባታችንን የብረት ቀንበር ይዞ ይመለሳል፤ ሕዝቡን በሐሰት እንዲታመኑ ስላስተማረ እንደሚሞት ለሐናንያ ይነግረዋል። ሞተም።
28 1በዚያ ዓመት፣ የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ በነገሠ መጀመሪያ፣ በአራተኛው ዓመት በአምስተኛው ወር፣ የጊባዖን ሰው የዐዙር ልጅ ነቢዩ ሐናንያ በካህናቱና በሕዝቡ ሁሉ ፊት በአባታችን ቤት እንዲህ አለኝ፦ 2“የሰማይ ሠራዊት እግዚአብሔር፣ የእስራኤል አምላክ እንዲህ ይላል፤ የባቢሎንን ንጉሥ ቀንበር ሰብሬአለሁ። 3የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ከዚህ ወደ ባቢሎን የወሰዳቸውን የእግዚአብሔርን ቤት ዕቃዎች ሁሉ በሁለት ዓመት ውስጥ ወደዚህ ስፍራ መልሼ አመጣለሁ። 4የይሁዳ ንጉሥ የዮአቄም ልጅ ኢኮንያንን፣ እንዲሁም ወደ ባቢሎን የተማረኩትን የይሁዳ ምርኮኞች ሁሉ ወደዚህ እመልሳለሁ፤ የባቢሎንን ንጉሥ ቀንበር እሰብራለሁና፤ ይላል እግዚአብሔር።”
5ነቢዩ ኤርምያስም በካህናቱና በአባታችን ቤት ቆመው በነበሩት ሕዝብ ሁሉ ፊት ነቢዩን ሐናንያን መለሰለት። 6ነቢዩ ኤርምያስም እንዲህ አለ፤ “አሜን! አባታችን እንዲሁ ያድርግ። የአባታችንን ቤት ዕቃዎችና ምርኮኞችን ሁሉ ከባቢሎን ወደዚህ ስፍራ በመመለስ፣ አንተ የተነበይኸውን ቃል ያጽናው። 7አሁን ግን ለአንተና ለዚህ ሕዝብ ሁሉ የምናገረውን ይህን ቃል ስማ፤ 8ከእኛ በፊት የነበሩት ነቢያት ከጥንት ጀምሮ በብዙ አሕዛብና በታላላቅ መንግሥታት ላይ ጦርነትን፣ ጥፋትንና ቸነፈርን ተነበዩ። 9ሰላምን የሚተነብይ ነቢይ ቃሉ በተፈጸመ ጊዜ ብቻ በእውነት ከአባታችን እንደ ተላከ ይታወቃል።”
10ከዚያም ነቢዩ ሐናንያ ቀንበሩን ከነቢዩ ከኤርምያስ ዐንገት ላይ አውርዶ ሰበረው፤ 11ሐናንያም ለሕዝቡ ሁሉ እንዲህ አለ፤ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ የባቢሎንን ንጉሥ የናቡከደነፆርን ቀንበር በሁለት ዓመት ውስጥ ከአሕዛብ ሁሉ ዐንገት ላይ እንዲሁ እሰብራለሁ።” ከዚያም ነቢዩ ኤርምያስ ሄደ።
12ሐናንያ ቀንበሩን ከነቢዩ ከኤርምያስ ዐንገት ላይ ከሰበረ በኋላ፣ የአባታችን ቃል ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፤
13“ሂድና ለሐናንያ እንዲህ ብለህ ንገረው፤ አባታችን እንዲህ ይላል፤ የእንጨት ቀንበር ሰበርህ፤ ነገር ግን በፋንታው የብረት ቀንበር ታበጃለህ። 14የሰማይ ሠራዊት አባት፣ የእስራኤል አባታችን እንዲህ ይላልና፤ የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን እንዲያገለግሉ በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ ዐንገት ላይ የብረት ቀንበር ጫንሁ፤ ያገለግሉታልም። የምድር አራዊትን እንኳ ሰጠሁት።”
15“ነቢዩ ኤርምያስም ነቢዩን ሐናንያን እንዲህ አለው፤ ‘ሐናንያ ሆይ፣ ስማ! አባታችን አልላከህም፤ ይህን ሕዝብ በሐሰት እንዲታመን አደረግህ።’ 16ስለዚህ አባታችን እንዲህ ይላል፤ በዚህ ዓመት ከምድር ላይ አስወግድሃለሁ፤ በአባታችን ላይ ዐመፅን ስለ ሰበክህ ትሞታለህ።”
17ነቢዩ ሐናንያም በዚያው ዓመት በሰባተኛው ወር ሞተ።