አባታችን የሮብዓምን ጦርነት አስቀረ
ሮብዓም ሰሜንን መልሶ ለማሸነፍ ሠራዊት ያሰባስባል፤ በአባታችን ቃልም ይከለከላል፤ ይህ ከእኔ ነው፤ ወደ ቤታችሁ ተመለሱ። በምትኩ የይሁዳን ከተሞች ያጠናክራል፤ በኢዮርብዓም የጥጃ መስገጃዎች የተባረሩ ካህናትና ሌዋውያንም ወደ እርሱ መጥተው መንግሥቱን ሦስት ዓመት ያጸኑታል።
11 1ሮብዓም ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ፣ ከእስራኤል ጋራ ተዋግቶ መንግሥቱን ለሮብዓም ለመመለስ የተመረጡ መቶ ሰማንያ ሺህ ተዋጊዎችን ከይሁዳና ከብንያም ቤት ሰበሰበ። 2ነገር ግን የአባታችን ቃል ወደ አባታችን ሰው ወደ ሳሚያስ እንዲህ ሲል መጣ፤
3“የይሁዳ ንጉሥ ለሰሎሞን ልጅ ለሮብዓም፣ በይሁዳና በብንያም ላሉ እስራኤላውያን ሁሉ እንዲህ በላቸው፤ 4አባታችን እንዲህ ይላል፤ ወደ ወንድሞቻችሁ አትውጡ፤ አትዋጉአቸውም። እያንዳንዳችሁ ወደየቤታችሁ ተመለሱ፤ ይህ ነገር ከእኔ ዘንድ ሆኗልና።” ስለዚህ የአባታችንን ቃል ታዘው ኢዮርብዓምን ለመውጋት ከመውጣት ተመለሱ።
ሮብዓም ይሁዳን አጸና
5ሮብዓም በኢየሩሳሌም ኖረ፤ በይሁዳም ለመከላከያ የሚሆኑ ከተሞችን ሠራ። 6ቤተ ልሔምን፣ ዔጣምን፣ ቴቁሔን፣ 7ቤትሱርን፣ ሶኮን፣ ዓዶላምን፣ 8ጌትን፣ ማሬሳን፣ ዚፍን፣ 9አዶራይምን፣ ለኪሶን፣ አዜቃን፣ 10ሦራን፣ ኤሎንንና ኬብሮንን ሠራ፤ እነዚህም በይሁዳና በብንያም የነበሩ የተመሸጉ ከተሞች ናቸው። 11ምሽጎቹንም አጸና፤ በውስጣቸውም አዛዦችን፣ የምግብ፣ የዘይትና የወይን ጠጅ ክምችትን አኖረ። 12በየከተማውም ጋሻዎችንና ጦሮችን አኖረ፤ እጅግም አበረታቸው። ስለዚህ ይሁዳና ብንያም የእርሱ ሆነው ቀሩ።
13በእስራኤል ሁሉ የነበሩ ካህናትና ሌዋውያን ከየአውራጃቸው ወደ እርሱ መጡ፤ 14ኢዮርብዓምና ልጆቹ የአባታችን ካህናት ሆነው ከማገልገል ስላገዱአቸው፣ ሌዋውያኑ መስኮቻቸውንና ንብረታቸውን ትተው ወደ ይሁዳና ወደ ኢየሩሳሌም ሄዱ። 15ለኰረብታ መስገጃዎች፣ ለፍየል ጣዖታትና ለሠራቸው የጥጃ ጣዖታት የራሱን ካህናት ሾመ። 16ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ፣ የእስራኤልን አምላክ አባታችንን ለመፈለግ ልባቸውን ያደረጉ ሰዎች፣ ለአባቶቻቸው አምላክ ለአባታችን መሥዋዕት ለማቅረብ ሌዋውያኑን ተከትለው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ። 17የይሁዳንም መንግሥት አጸኑ፤ ሦስት ዓመትም የሰሎሞንን ልጅ ሮብዓምን ደገፉ፤ ሦስት ዓመት በዳዊትና በሰሎሞን መንገድ ተመላልሰዋልና።
የሮብዓም ቤተ ሰብ
18ሮብዓምም ማህላትን አገባ፤ እርሷም የዳዊት ልጅ የኢያሪሞትና የእሴይ ልጅ የኤልያብ ልጅ የአቢካይል ልጅ ነበረች። 19እርሷም ኢዩሻን፣ ሸማርያንና ዛሃምን ወለደችለት። 20ከእርሷ በኋላ የአቤሴሎምን ልጅ መዓካን አገባ፤ እርሷም አብያን፣ አታይን፣ ዚዛንና ሰሎሚትን ወለደችለት። 21ሮብዓም ዐሥራ ስምንት ሚስቶችና ስድሳ ቁባቶች ነበሩት፤ ሃያ ስምንት ወንዶች ልጆችና ስድሳ ሴቶች ልጆችም ወለደ፤ ነገር ግን የአቤሴሎምን ልጅ መዓካን ከሌሎች ሚስቶቹና ቁባቶቹ ሁሉ አብልጦ ይወድ ነበር። 22ሮብዓምም ሊያነግሠው አስቦ የመዓካን ልጅ አብያን በወንድሞቹ መካከል ዋና መሪ አደረገው። 23በጥበብም ሠራ፤ ከልጆቹም አንዳንዶቹን በይሁዳና በብንያም አውራጃዎች ሁሉ፣ በየተመሸገው ከተማ በተናቸው፤ ብዙ ቀለብም ሰጣቸው፤ ብዙ ሚስቶችንም ፈለገላቸው።