የአባታችን ታሪክ ይጀምራል፦ ከአዳም እስከ አብርሃም
የእስራኤል ታሪክ በዳዊት ዘመነ መንግሥት በኩል እንደገና ይተረካል፤ በማእከሉም አምልኮ አለ። በትውልድ ሐረጎቹና በመዝሙሮቹ መካከል አብ ለልጁ የሰጠው ተስፋና እርሱን እንድንፈልግ የቀረበ ግብዣ ተሸምኖ ይገኛል።
1 1አዳም፣ ሴት፣ ኤኖስ፣ 2ቃይናን፣ መላልኤል፣ ያሬድ፣ 3ሄኖክ፣ ማቱሳላ፣ ላሜሕ፣ 4ኖኅ፣ ሴም፣ ካም፣ ያፌት።
5የያፌት ልጆች፦ ጎሜር፣ ማጎግ፣ ማዳይ፣ ያዋን፣ ቶቤል፣ ሞሳሕ፣ ቲራስ። 6የጎሜር ልጆች፦ አስከናዝ፣ ዲፋት፣ ቶጋርማ። 7የያዋን ልጆች፦ ኤሊሳ፣ ተርሴስ፣ ኪቲም፣ ሮዳኒም።
8የካም ልጆች፦ ኩሽ፣ ምጽራይም፣ ፉጥ፣ ከነዓን። 9የኩሽ ልጆች፦ ሳባ፣ ኤውላጥ፣ ሳብታ፣ ራዕማ፣ ሳብካ። የራዕማ ልጆች፦ ሳባና ዳዳን። 10ኩሽ ናምሩድን ወለደ፤ እርሱም በምድር ላይ ኀያል ለመሆን የመጀመሪያው ነበር። 11ምጽራይም ሉዳውያንን፣ ዐናማውያንን፣ ለሃባውያንን፣ ናፍታማውያንን፣ 12ጲያትሮሳውያንን፣ ፍልስጥኤማውያን የወጡባቸውን ከስሉሃውያንን፣ ከፍታራውያንን ወለደ። 13ከነዓን በኵር ልጁን ሲዶናን፣ ኬጥንም፣ 14ኢያቡሳውያንንም፣ አሞራውያንን፣ ጌርጌሳውያንን፣ 15ኤዊያውያንን፣ አርካውያንን፣ ሲናውያንን፣ 16አራዳውያንን፣ ጸማራውያንን፣ ሐማታውያንን ወለደ።
17የሴም ልጆች፦ ኤላም፣ አሱር፣ አርፋክስድ፣ ሉድ፣ አራም፤ የአራም ልጆችም፦ ዑፅ፣ ሑል፣ ጌቴር፣ ሞሳሕ። 18አርፋክስድ ሳላን ወለደ፤ ሳላም ዔቦርን ወለደ። 19ዔቦር ሁለት ልጆች ነበሩት፤ ምድር በእርሱ ዘመን ስለ ተከፋፈለች የአንዱ ስም ፋሌቅ ተባለ፤ የወንድሙም ስም ዮቅጣን ነበር። 20ዮቅጣን አልሞዳድን፣ ሣሌፍን፣ አሰርሞትን፣ ያራሕን፣ 21አዶራምን፣ ኡዛልን፣ ዲቅላን፣ 22ዔባልን፣ አቢማኤልን፣ ሳባን፣ 23ኦፊርን፣ ኤውላጥን፣ ዮባብን ወለደ። እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ልጆች ነበሩ። 24ሴም፣ አርፋክስድ፣ ሳላ፣ 25ዔቦር፣ ፋሌቅ፣ ራግው፣ 26ሴሮህ፣ ናኮር፣ ታራ፣ 27አብራም፣ እርሱም አብርሃም ነው።
የአብ ተስፋ በአብርሃም በኩል
28የአብርሃም ልጆች፦ ይስሐቅና እስማኤል። 29የትውልዳቸው መዝገብ ይህ ነው፦ የእስማኤል በኵር ልጅ ናባዮት፤ ቀጥሎም ቄዳር፣ አድብኤል፣ ሚብሳም፣ 30ሚስማ፣ ዱማ፣ ማሳ፣ ሐዳድ፣ ቴማ፣ 31የጡር፣ ናፊስ፣ ቄድማ። እነዚህ የእስማኤል ልጆች ናቸው።
32የአብርሃም ቁባት ኬጡራ ዘምራንን፣ ዮቅሻንን፣ ሜዳንን፣ ምድያንን፣ እሽባቅን፣ ሱሐን ወለደች። የዮቅሻን ልጆች፦ ሳባና ዳዳን። 33የምድያን ልጆች፦ ጌፋ፣ ዔፌር፣ ሄኖሕ፣ አቢዳ፣ ኤልዳዓ። እነዚህ ሁሉ የኬጡራ ልጆች ነበሩ።
34አብርሃም ይስሐቅን ወለደ። የይስሐቅ ልጆች፦ ዔሳውና እስራኤል።
የዔሳው ልጆች
35የዔሳው ልጆች፦ ኤሊፋዝ፣ ራጉኤል፣ ይዑስ፣ ይዕላም፣ ቆራ። 36የኤሊፋዝ ልጆች፦ ቴማን፣ ኦማር፣ ጸፊ፣ ጋዕታም፣ ቄናዝ፣ ቲምናና ዓማሌቅ። 37የራጉኤል ልጆች፦ ነሃት፣ ዛራ፣ ሻማ፣ ሚዛ።
38የሴይር ልጆች፦ ሎጣን፣ ሦባል፣ ጽብዖን፣ ዓና፣ ዲሶን፣ ኤጼር፣ ዲሳን። 39የሎጣን ልጆች፦ ሖሪና ሆማም፤ የሎጣንም እኅት ቲምና ነበረች። 40የሦባል ልጆች፦ ዓልያን፣ ማናሃት፣ ዔባል፣ ሸፊ፣ ዖናም። የጽብዖን ልጆች፦ አያህና ዓና። 41የዓና ልጅ፦ ዲሶን። የዲሶን ልጆች፦ ሐምራን፣ እሽባን፣ ይትራን፣ ከራን። 42የኤጼር ልጆች፦ ቢልሃን፣ ዛዓዋን፣ ያዓቃን። የዲሳን ልጆች፦ ዑፅና አራን።
43እስራኤላውያንን የሚገዛ ንጉሥ ሳይኖር በፊት በኤዶም ምድር የነገሡ ነገሥታት እነዚህ ናቸው፦ የቢዖር ልጅ ቤላ፤ የከተማውም ስም ዲንሐባ ነበር። 44ቤላ በሞተ ጊዜ ከባሶራ የመጣው የዛራ ልጅ ዮባብ በእርሱ ፈንታ ነገሠ። 45ዮባብ በሞተ ጊዜ ከቴማናውያን ምድር የመጣው ሐሳም በእርሱ ፈንታ ነገሠ። 46ሐሳም ሞተ፤ በሞዓብ አገር ምድያንን ያሸነፈው የበዳድ ልጅ ሐዳድ በእርሱ ፈንታ ነገሠ፤ የከተማውም ስም ዓዊት ነበር። 47ሐዳድ በሞተ ጊዜ ከማስሬቃ የመጣው ሳምላ በእርሱ ፈንታ ነገሠ። 48ሳምላ በሞተ ጊዜ በወንዙ ዳር ከምትገኘው ሮብሆት የመጣው ሳኦል በእርሱ ፈንታ ነገሠ። 49ሳኦል በሞተ ጊዜ የዓክቦር ልጅ ብዔልሃናን በእርሱ ፈንታ ነገሠ። 50ብዔልሃናን ሞተ፤ ሐዳድ በእርሱ ፈንታ ነገሠ። የከተማውም ስም ፓዒ ነበር፤ ሚስቱም የሜዛሃብ ልጅ የሆነችው የማጥሬድ ልጅ ሜጤቤል ነበረች። 51ሐዳድም ሞተ። የኤዶም የጎሳ አለቆች እነዚህ ነበሩ፦ አለቃ ቲምና፣ አለቃ ዓልያ፣ አለቃ የቴት፣ 52አለቃ ኦሆሊባማ፣ አለቃ ኤላ፣ አለቃ ፊኖን፣ 53አለቃ ቄናዝ፣ አለቃ ቴማን፣ አለቃ ሚብጻር፣ 54አለቃ መግዲኤል፣ አለቃ ዒራም። እነዚህ የኤዶም የጎሳ አለቆች ነበሩ።